本书并非出自上帝启示,且不属于基督教正典或犹太教塔纳赫的一部分。仅为历史与研究目的而展示。 查看完整说明 መጽሐፈ ሲራክ 37:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ሴትን ስለጣውንቷ፥ ፊሪን ስለ ጦርነት፥ ነጋዴን ስለዋጋ፥ ሸማችን ስለገበያ፥ ባለጌን ስለ ውለታ፥ ራስ ወዳዱን ስለ ደግነት፥ ሰነፉን ስለ ሥራ፥ ዳተኛውን ስለ ሥራው ፍጻሜ፥ ሀኬተኛውን አገልገይ ስለ አስቸጋሪው ሥራ አትጠይቃቸው። ከእነርሱ የሚመጣውንም ምክር አትቀበል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ከሴት ጋር ስለሚያስቀናት ነገር አትናገር፤ ስለ ጦርነትም ከፈሪ ሰው ጋር አትማከር። ስለ ትርፍም ከሻጭ ጋር አትማከር፤ ስለ ንግድ ነገርም ከነጋዴ ጋር አትማከር። ስለ ምጽዋትም ከንፉግ ሰው ጋር አትማከር። ዋጋን ስለ መመለስም ከከዳተኛ ጋር አትማከር፤ ስለ ሥራም ከሰነፍ ሰው ጋራ አትማከር፤ ሥራ ስለሚፈጸምበት ዓመትም ከምንደኛ ጋር አትማከር። ስለ ጥበብም ከአላዋቂ ሰው ጋር አትማከር፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ስለዚህ ነገር የምትማከረው አይኑር። 参见章节 |