Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሩት 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የአጫጆቹም አዛዥ፦ “ይህችማ ከሞዓብ ምድር ከናዖሚን ጋር የመጣች ሞዓባዊቱ ብላቴና ናት፥” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የዐጫጆቹም አለቃ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ከኑኃሚን ጋራ ከሞዓብ ምድር ተመልሳ የመጣች ሞዓባዊት ናት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሰውየውም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እርስዋ ናዖሚን ተከትላ ከሞአብ አገር የመጣች ሞአባዊት ናት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የአጫጆቹም አዛዥ፦ ይህችማ ከሞዓብ ምድር ከኑኃሚን ጋር የመጣች ሞዓባዊቱ ቆንጆ ናት፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የአጫጆቹም አዛዥ “ይህችማ ከሞዓብ ምድር ከኑኃሚን ጋር የመጣች ሞዓባዊቱ ቆንጆ ናት፤

参见章节 复制




ሩት 2:6
10 交叉引用  

አብራምም፦ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምንን ትሰጠኛለህ? እኔም ያለ ልጅ እሄዳለሁ፥ የቤቴም መጋቢ የደማስቆ ሰው ይህ ኤልዔዘር ነው አለ።


አብርሃምም ሎሌውን የቤቱን ሽማግሌ የከብቱን ሁሉ አዛዥ አለው፦


ዮሴፍ በእርሱ ዘንድ ሞገስ አገኘ፤ የቅርብ አገልጋዩም ሆነ። ጲጥፋራ በቤቱ ላይ ሾመው፤ ያለውንም ሀብት ሁሉ በኀላፊነት ሰጠው።


በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ ሹሙን ‘ሠራተኞቹን ጥራና ኋላ ከመጡት ጀምረህ መጀመሪያ እስከመጡት ድረስ ደመወዝ ስጣቸው፤’ አለው።


“ለቤተሰቦቹ ምግባቸውን በጊዜው እንዲሰጣቸው፥ ጌታው በቤተሰቦቹ ላይ የሾመው ታማኝና ብልህ ባርያ ማን ነው?


ሩት ግን እንዲህ አለች፦ “እንድተውሽ ተለይቼሽም እንድመለስ አታስገድጅኝ፤ በምትሄጅበት እሄዳለሁ፥ በምታድሪበትም አድራለሁ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፤


ስለዚህ ሁለቱም እስከ ቤተልሔም ድረስ ሄዱ። ወደ ቤተልሔምም በደረሱ ጊዜ፥ ያገሩ ሰዎች ሁሉ ታወኩ ስለ እነርሱ፥ ሴቶቹም፦ “ይህች ናዖሚን ናትን?” አሉ።


ስለዚህ ናዖሚ፥ ከሞአባዊት ምራትዋ ከሩት ጋር፥ ከሞዓብ አገር ተመለሰች። የገብስም መከር መሰብሰቢያ ጅማሬ ላይ ቤተልሔም መጡ።


ቦዔዝም በአጫጆች ላይ አዛዥ የነበረውን አገልጋዩን፦ “ይህች ብላቴና የማን ናት?” አለው።


“እርሷም፦ ‘ከአጫጆቹ በኋላ በነዶው መካከል እንድቃርምና እንድለቅም፥ እባክህ፥ ፍቀድልኝ’ ብላ፥ መጣች፤ ከማለዳም ጀምራ እስከ አሁን ስትቃርም ቆይታለች፤ በቤትም ጥቂት ጊዜ እንኳ አላረፈችም” አለው።


跟着我们:

广告


广告