Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሩት 1:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የሰውዬው ስም ኤሊሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ናዖሚ፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፥ እነርሱም የቤተልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ፥ በዚያም ተቀመጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የሰውየው ስም አሊሜሌክ፣ የሚስቱ ኑኃሚን፣ የሁለቱም ወንዶች ልጆቹ ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበር። እነርሱም የይሁዳ ቤተ ልሔም ኤፍራታውያን ሲሆኑ፣ ወደ ሞዓብ አገር ሄደው በዚያ ኖሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የሰውዬው ስም ኤቤሜሌክ፥ የሚስቱ ስም ናዖሚ፥ የሁለቱ ልጆች ስም ማሕሎንና ኬሌዎን ይባል ነበር፤ በትውልዱ ኤፍራታዊ ሆኖ በቤተልሔም ከተማ የሚኖር ነበር፤ እርሱም ከቤተሰቡ ጋር ወደ ሞአብ አገር ሄዶ ኖረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፥ የቤተ ልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፤ የቤተ ልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።

参见章节 复制




ሩት 1:2
11 交叉引用  

ራሔልም ሞተች፥ ወደ ኤፍራታ በምትወስድም መንገድ ተቀበረች፥ እርሷም ቤተልሔም ናት።


ስለዚህ ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ ከዚህ በኋላ የቀሩት ወንድሞቹ ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ።


በይሁዳ ምድር፥ በይሁዳ ነገድ መካከል በቤተልሔም የሚኖር አንድ ሌዋዊ ወጣት ነበር።


በዚያን ቀን ሞዓብ በእስራኤል ድል ሆነች፤ ምድሪቱም ለሰማንያ ዓመት ሰላም አገኘች።


የናዖሚም ባል ኤሊሜሌክ ሞተ፥ እርሷም ከሁለቱ ልጆችዋ ጋር ቀረች።


መሐሎንና ኬሌዎን ሁለቱም ሞቱ፥ ሴቲቱም ሁለቱን ልጆችዋንና ባልዋን አጥታ ብቻዋን ቀረች።


ለናዖሚም በባልዋ የሚዛመዳት ሰው ከኤሊሜሌክ ወገን የሆነ ስሙ ቦዔዝ የተባለ ኃያል ሰው ነበረ።


ቦዔዝም ሽማግሌዎችንና ሕዝቡን ሁሉ፦ “ለኤሊሜሌክና ለኬሌዎን ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከናዖሚን እጅ እንደ ገዛሁ እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ።


በተራራማው በኤፍሬም አገር በአርማቴም መሴፋ የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊዩ ልጅ፥ የቶሑ ልጅ፥ የናሲብ ልጅ ሲሆን ከኤፍሬም ነገድ ነበረ።


ዳዊት፥ በይሁዳ ስምንት ወንዶች ልጆች የነበሩት፥ የቤተልሔሙ ሰው የኤፍራታዊው የእሴይ ልጅ ነበር። እሴይም በሳኦል ዘመን ያረጀና ዕድሜው የገፋ ሰው ነበር።


እስራኤልና ፍልስጥኤማውያን ቦታ ቦታቸውን ይዘው ፊት ለፊት ተፋጠው ይጠባበቁ ነበር።


跟着我们:

广告


广告