ሮሜ 9:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 ለምን? ምክንያቱም በእምነት ሳይሆን በሥራ እንደሆነ ስለቆጠሩት ነው፤ ስለዚህ በማሰናከያ ድንጋይ ተሰናከሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ይህ ለምን ሆነ? በእምነት ሳይሆን በሥራ እንደ ሆነ አድርገው በመቍጠር ስለ ተከታተሉት ነው፤ እነርሱም፣ “በማሰናከያው ድንጋይ” ተሰናከሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 “ስለምን ወደ ጽድቅ አልደረሱም?” ቢባል እነርሱ ጽድቅን ለማግኘት የፈለጉት በእምነት ሳይሆን በሥራ ስለ ሆነ ነው፤ ስለዚህ በማሰናከያ ድንጋይ ተሰናከሉ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 ይህስ ስለምን ነው? ጽድቃቸው የኦሪትን ሥራ በመሥራት እንጂ በእምነት ስለ አልሆነ ነው፤ የእንቅፋት ድንጋይ አሰነካከላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32-33 ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፤ እነሆ፥ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደ ተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ። 参见章节 |