ሮሜ 7:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ስለዚህ ባሏ በሕይወት እያለ ሌላ ባል ብታገባ አመንዝራ ትባላለች። ባሏ ቢሞት ግን ከሕጉ ነፃ ናት፥ ሌላ ባል ብታገባ አመንዝራ አይደለችም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ነገር ግን ባሏ በሕይወት እያለ ሌላ ሰው ብታገባ አመንዝራ ትባላለች፤ ባሏ ቢሞት ግን ሌላ ሰው ብታገባም እንኳ፣ ከዚያ ሕግ ነጻ ትሆናለች፤ አመንዝራ አትባልም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ስለዚህ ባልዋ በሕይወት እያለ ሌላ ወንድ ብታገባ አመንዝራ ትባላለች። ባልዋ ከሞተ ግን ከእርሱ ጋር ከታሰረችበት ሕግ ነጻ ትወጣለች፤ ሌላ ወንድ ብታገባም አመንዝራ አይደለችም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ስለዚህ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትሆናለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕግ ነፃ ወጥታለች፤ ለሌላ ወንድ ብትሆንም አመንዝራ አትባልም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ስለዚህ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕጉ አርነት ወጥታለችና ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አይደለችም። 参见章节 |