Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሮሜ 11:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የእነርሱ መጣል ለዓለም እርቅን ካስገኘ፥ ተቀባይነት ማግኘታቸውማ ከሞት መነሣት ነው ከማለት በቀር ምን መሆን ይችላል?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የእነርሱ መተው ለዓለም ዕርቅን ካስገኘ፣ ተቀባይነት ማግኘታቸውማ ከሞት መነሣት ነው ከማለት በቀር ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እግዚአብሔር እነርሱን በጣላቸው ጊዜ ሌላው የዓለም ሕዝብ ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቀ እግዚአብሔር እነርሱን በሚቀበላቸው ጊዜ ምን የሚሆን ይመስላችኋል? ይህማ ከሞት እንደ መነሣት ያኽል ነው!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የእ​ነ​ርሱ መው​ጣት ለዓ​ለም ዕርቅ ከሆነ ይል​ቁ​ንም መመ​ለ​ሳ​ቸው ምን ይሆን? ከሙ​ታን በመ​ነ​ሣት የሚ​ገኝ ሕይ​ወት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የእነርሱ መጣል ለዓለም መታረቅ ከሆነ ከሙታን ከሚመጣ ሕይወት በቀር መመለሳቸው ምን ይሆን?

参见章节 复制




ሮሜ 11:15
14 交叉引用  

ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም።’ ደስ ይላቸውም ጀመር።


ዳሩ ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበረ፤ ሕያው ስለ ሆነ ጠፍቶም ነበር፤ ስለ ተገኘ ደስ እንዲለን ፍሥሐም እንድናደርግ ይገባናል’።”


በእምነት የደከመውንም አከራካሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሳትፈርዱበት ተቀበሉት።


የሚበላ የማይበላውን አይናቀው፤ የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፤ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።


በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል፥ በዘመን ፍጻሜ እንዲሆን እንዳቀደው፥


ከሦስቱ ቀን ተኩልም በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው፤ በእግሮቻቸውም ቆሙ፤ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው።


跟着我们:

广告


广告