Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 89:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው፥ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ኀያል ነህ፤ ታማኝነትህም ከብቦሃል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እንደ አንተ ያለ ኀያል ማነው! አንተ በሁሉ ነገር ታማኝ ነህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በፊ​ትህ አስ​ቀ​መ​ጥህ፥ ዓለ​ማ​ች​ንም በፊ​ትህ ብር​ሃን ነው።

参见章节 复制




መዝሙር 89:8
19 交叉引用  

እንዲህም አልሁ፦ ታላቅና የተፈራ አምላክ፥ ለሚወድዱትና ትእዛዙን ለሚጠብቁ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የሚጠብቅ፥ የሰማይ አምላክ ጌታ ሆይ፥


ከሰሜን ወርቅ የሚመስል ጌጠኛ ብርሃን ይወጣል፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስፈራ ግርማ አለ።


የኃይል ነገር ከሆነ፥ ኃያሉ እርሱ እነሆ፥ የፍርድ ነገር ከሆነም፥ የችሎቱን ጊዜ ወሳኙ ማን ነው? ይላል።


ጌታችን ታላቅ ነው፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር ስፍር የለውም።


ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? ጌታ ነው፥ ብርቱና ኃያል፥ ጌታ ነው፥ በሰልፍ ኃያል።


አጥንቶቼ ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? ችግረኛን ከሚቀማው እጅ፥ ችግረኛንና ድሀውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።


አቤቱ፥ ጽድቅህ እስከ አርያም ይደርሳል፥ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል፥ አምላክ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?


ጌታ አምላክ ፀሐይና ጋሻ ነው፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፥ ጌታ በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያስቀራቸውም።


ሰሜንንና ደቡብን አንተ ፈጠርህ፥ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል።


አቤቱ፥ ሰማያት ድንቅ ሥራህን ታማኝነትህንም፥ በቅዱሳን ማኅበር፥ ያመሰግናሉ።


አሁንም በምድር ሁሉ ላይ የሚጸናውን የጥፋት ትእዛዝ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና እስራት እንዳይጸናባችሁ አታፊዙ።


‘አቤቱ ጌታ ሆይ! ወዮ! እነሆ፥ በእውነት አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ለአንተም ከቶ የሚሳንህ ምንም ነገር የለም።


ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።’


ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት፥ ዓለታቸው እንደ እኛ ዓለት አይደለም።


ጌታ አምላክህ፥ ታላቅና የሚያስፈራ አምላክ፥ በመካከልህ ነውና በእነርሱ የተነሣ ልትደናገጥ አይገባም።


“የአማልክት አምላክ ጌታ! የአማልክት አምላክ ጌታ! እርሱ አውቆታል፥ እስራኤልም ራሱ ይወቀው፤ በጌታ ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደሆነ ዛሬ አታድነን፤


ታዲያ የጌታን ቃል ለምን አልታዘዝህም? ለምርኮውስ ተስገብግበህ በጌታ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ለምን አደረግህ?”


እንደ ጌታ ያለ ቅዱስ የለም፥ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤ አምላካችንን የሚመስልም ዓለት የለም።


跟着我们:

广告


广告