Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 64:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከክፉዎች ደባ፥ ከዓመፀኞችም ብዛት ሰውረኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እነርሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤ መርዘኛ ቃላቸውንም እንደ ፍላጻ ያነጣጥራሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እነርሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤ እጅግ የከፋ ቃላትን እንደ ፍላጻ አነጣጥረው ይወረውራሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የዐ​መ​ፀ​ኞች ነገር በረ​ታ​ብን፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ን​ንስ አንተ ይቅር ትላ​ለህ።

参见章节 复制




መዝሙር 64:3
9 交叉引用  

እነሆ ክፉዎች ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ ዘንድ።


ከሰወሩብኝ ወጥመድ፥ ዓመፅንም ከሚያደርጉ ሰዎች ዕንቅፋት ጠብቀኝ።


ከሰማይ ልኮ አዳነኝ፥ ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው፥ እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነቱን ላከ።


አምላክ ሆይ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፥ የአንበሶቹን መንጋጋቸውን አድቅቅ።


እንደሚዋጋ ሰይፍ የሚለፈልፍ ሰው አለ፥ የጠቢባን ምላስ ግን ጤና ነው።


ድሆችን ከምድር ላይ ችግረኞችንም ከሰው መካከል ለማጥፋትና ለመጨረስ ጥርሶቹ ሰይፍ መንጋጎቹም ካራ የሆኑ ትውልድ አለ።


በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም የሚነሣብሽን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የጌታ አገልጋዮች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል ጌታ።


ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።


跟着我们:

广告


广告