Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 37:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው፥ በእርምጃውም አይሰናከልም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤ አካሄዱም አይወላገድም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 የአምላኩም ሕግ በልቡ ነው፤ እግሩም አይደናቀፍም።

参见章节 复制




መዝሙር 37:31
20 交叉引用  

እግሬ ዱካውን ተከትሎአል፥ መንገዱንም ጠብቄአለሁ፥ ከመስመር አልወጣሁም።


ነገር ግን በጌታ ሕግ ደስ የሚለው፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያስብ።


አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።


ለዘለዓለም ለእኔ ነውና ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ።


እግርህ እንዲናወጥ አይፈቅድም፥ የሚጠብቅህም አይተኛም።


እግሮች እንዳይናወጡ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።


መንገዱን በወደደ ጊዜ፥ የሰው አካሄድ በጌታ ይጸናል።


በዚያን ጊዜ እንዲህ አልሁ፦ “እነሆ፥ መጣሁ፥ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፥


አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።”


ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደረሰ፥ አልረሳንህም፥ ኪዳንህንም አልወነጀልንም።


እኔ ግን እግሮቼ ሊሰናከሉ፥ በአረማመዴም ልወድቅ ትንሽ ቀረኝ።


የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፥ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል።


ያስተምረኝም ነበር እንዲህም ይለኝ ነበር፦ “ልብህ ቃሌን በጥብቅ ይያዘው፥ ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ።


ጽድቅን የምታውቁ ሕጌም በልባችሁ ያለ ሕዝብ ሆይ፥ ስሙኝ፤ የሰውን ተግዳሮት አትፍሩ፥ በስድባቸውም አትደንግጡ።


ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የማደርገው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


በባሻን ባሉጦች መቅዘፊያሽን ሠሩ፤ በዝሆን ጥርስ ከታሻበ ከኪቲም ደሴቶች ዛፍ ወለልሽን ሠርተዋል።


ዛሬ እኔ የማዝህ እነዚህን ቃላትም በልብህ አኑር።


ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል።


跟着我们:

广告


广告