Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 30:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥ ወደ ጉድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እናንተ የምትታመኑት፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ቅዱስ ስሙንም አወድሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ለእርሱ ታማኞች አገልጋዮች የሆናችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን በዝማሬ አመስግኑት! ለቅዱስ ስሙም ምስጋና አቅርቡለት!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አቤቱ፥ አንተ ረዳቴ ነህና ከሰ​ወ​ሩ​ብኝ ከዚች ወጥ​መድ አው​ጣኝ።

参见章节 复制




መዝሙር 30:4
16 交叉引用  

በጌታም ታቦት ፊት እንዲያገለግሉ፥ የእስራኤልንም አምላክ ጌታን እንዲወድሱት፥ እንዲያመሰግኑትና እንዲያከብሩትም ከሌዋውያን ወገን ሾመ።


ቃሉን ላከ ፈወሳቸውም፥ ከአዘቅትም አዳናቸው።


ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፥ ጻድቃንህም ደስ ይበላቸው።


የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ የቅዱሳኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል። ሃሌ ሉያ።


የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ወደ አንተ እጠራለሁ፥ ዝም ብትለኝ ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልመስል፥ አንተ ዓለቴ ሆይ፥ ዝም አትበለኝ።


ጻድቃን ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ፥ ልባችሁም የቀና ሁላችሁ፥ እልል በሉ።


“ከእኔ ጋር በመሥዋዕት ኪዳን ያቆሙትን ቅዱሳኑን ሰብስቡልኝ” ይላል።


ጽኑ ፍቅርህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥ ነፍሴንም ከታችኛይቱ ሲኦል አድነሃታልና።


ጻድቃን፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ፥ የማይረሳውን ቅድስናም አወድሱ።


ከአማልክት መካከል ጌታ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና ባለግርማ፥ በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?


እርስ በርሳቸው በመቀባበልም “ቅዱስ፤ ቅዱስ፤ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለች” ይሉ ነበር።


አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” ከማለት ቀንና ሌሊት አያርፉም ነበር።


ጌታ ይገድላል፤ ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፤ ከሲኦልም ያወጣል።


跟着我们:

广告


广告