23 አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ፥ ፈትነኝ መንገዴንም እወቅ፥
23 እግዚአብሔር ሆይ፤ መርምረኝ፤ ልቤንም ዕወቅ፤ ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ፤
23 አምላክ ሆይ! መርምረኝ፤ ልቡናዬንም ዕወቅ፤ ፈትነኝ፤ ሐሳቤንም ዕወቅ።
ጌታ በተቀደሰው መቅደሱ ነው፥ ጌታ፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፥ ዐይኖቹ ይመለከታሉ፥ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
ጌታ ጻድቅንና ክፉን ይመረምራል፥ ዓመፃ የሚወደውን ግን ነፍሱ ትጠላለች።
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ መረመርኸኝ፥ አወቅኸኝም።
ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፥ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም።
አቤቱ፥ ፈትነኝ መርምረኝም፥ ኩላሊቴንና ልቤን መርምር።
ማቅለጫ ለብር፥ ከውር ለወርቅ ነው፥ ጌታ ግን ልብን ይፈትናል።
ነገር ግን ኩላሊትንና ልብን የምትመረምር በቅንም የምትፈርድ አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ! ሙግቴን ገልጬልሃለሁና በእነርሱ ላይ የሚሆነውን በቀልህን ልይ።
አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።
በመጨረሻም መልካም ነገር ሊያደርግልህ፥ ሊፈትንህ ሊያዋርድህም አባቶችህ ያላወቁትን መና በምድረ በዳ ያበላህን፥
ጌታ አምላክህ ሊያስጨንቅህ፥ ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ፥ በልብህ ያለውን ያውቅ ዘንድ ሊፈትንህ፥ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስታውስ።
በዚህም በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ ነው።