Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 119:73 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

73 እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም፥ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ትእዛዛትህንም እማራለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

73 እጆችህ ሠሩኝ፤ አበጃጁኝም፤ ትእዛዞችህን እንድማር ማስተዋልን ስጠኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

73 እጆችህ ሠሩኝ፤ አበጃጁኝም፤ ትእዛዞችህን እማር ዘንድ አስተዋይነትን ስጠኝ።

参见章节 复制




መዝሙር 119:73
17 交叉引用  

ብቻ የአምላክህን የጌታን ሕግ እንድትጠብቅ ጌታ ጥበብንና ማስተዋልን ይስጥህ፥ በእስራኤልም ላይ ያሰልጥንህ።


እንዲሁም ኪራም እንዲህ አለ፦ “ሰማይንና ምድርን የፈጠረ፥ ለጌታም ቤተ መቅደስ ለመንግሥቱም ቤተ መንግሥት እንዲሠራ ጥበበኛና ብልሃተኛ አስተዋይም ልጅ ለንጉሡ ለዳዊት የሰጠ የእስራኤል አምላክ ጌታ ቡሩክ ይሁን።


እኔን በማኅፀን የፈጠረ እርሱንስ የፈጠረው አይደለምን? በማኅፀንስ ውስጥ የሠራን አንድ አይደለንምን?”


ነገር ግን በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጣል።


ጌታ እርሱ አምላክ እንደሆነ እወቁ፥ እርሱ ሠራን፥ እኛም የእርሱ ነን፥ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን።


የጥበብ መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥ የሚያደርጓትም ሁሉ ደኅና ማስተዋልን ያገኛሉ፥ ውዳሴውም ለዘለዓለም ይኖራል።


እኔ ባርያህ ነኝ፥ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ምስክርህንም አውቃለሁ።


ምስክርህ ለዘለዓለም ጽድቅ ነው፥ እንዳስተውል አድርገኝ፥ በሕይወትም አኑረኝ።


አቤቱ፥ ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትቅረብ፥ እንደ ቃልህም አስተዋይ አድርገኝ።


እንዳስተውል አድርገኝ፥ ሕግህንም እንድጠብቅ፥ በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ።


ጌታ ብድራትን ይመልስልኛል፥ አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ ለዘለዓለም ነው፥ አቤቱ፥ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል።


ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፥ በፈጠረን በእርሱ በጌታ ፊት እንበርከክ፥


ጌታ በሁሉ ነገር ማስተዋልን ይሰጥሃልና የምለውን ደኅና አድርገህ አሰላስል።


የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉ በሰላም ይዘራል።


የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ፥ እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነት በሆነው በእርሱ እንኖራለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።


跟着我们:

广告


广告