166 አቤቱ፥ ማዳንህን ተስፋ አደርግሁ፥ ትእዛዛትህንም ጠበቅሁ።
166 እግዚአብሔር ሆይ፤ ማዳንህን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ትእዛዝህንም እፈጽማለሁ።
166 እግዚአብሔር ሆይ! አዳኝነትህን በተስፋ እጠባበቃለሁ፤ ትእዛዞችህንም እፈጽማለሁ።
ጌታ ሆይ፥ መድኃኒትህን እጠብቃለሁ።
አቤቱ፥ ማዳንህን ናፈቅሁ፥ ሕግህም ተድላዬ ነው።
ነፍሴ መድኃኒትህን ናፈቀች፥ በቃልህም ታመንሁ።
ፍሩ፥ ኃጢአትንም አትሥሩ፥ በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ አስቡ፥ ዝምም በሉ።
ምስጋናን የሚሠዋ ያከብረኛል፥ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።
ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።
ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር እንደሆነ ወይንም እኔ ከራሴ የምናገር እንደሆነ ያውቃል።