27 አቤቱ፥ እጅህ ይህች መሆኗን፥ አንተም ይህንን እንዳደረግህ ይወቁ።
27 እግዚአብሔር ሆይ፤ እጅህ ይህን እንዳደረገች፣ አንተም ይህን እንደ ፈጸምህ ይወቁ።
27 የምታድነኝ አንተ ብቻ እንደ ሆንክ ጠላቶቼ እንዲያውቁ አድርግ።
ይህ ዕዝራ ከባቢሎን መጣ፥ የእስራኤል አምላክ ጌታ ለሙሴ በሰጠው ሕግ ችሎታ ያለው ጸሐፊ ነበረ፤ የአምላኩ የጌታ እጅ በእርሱ ላይ ስለ ነበረች ንጉሡ የጠየቀውን ነገር ሁሉ ሰጠው።
እንዲህም ሆነ፦ ጠላቶቻችን ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙሪያችን የነበሩ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፥ ዓይናቸውም እያየ ብዙ ውድቀት ሆነ፥ ይህ ሥራ በአምላካችን እንደ ተከናወነ አወቁ።
ሰው ሁሉ ሥራውን ያውቅ ዘንድ የሰውን ሁሉ እጅ ያትማል።
በዚያን ጊዜ አፋችን በሳቅ፥ አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፥ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ፦ ታላቅ ነገርን አደረገላቸው ተባለ።
በሕዝቤና በሕዝብህ መካከል ልዩነት አደርጋለሁ፤ ይህም ምልክት ነገ ይሆናል።’”
“በእነዚህ ሰዎች ምን እንሥራ? የታወቀ ምልክት በእነርሱ እጅ እንደ ተደረገበኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ተገልጦአልና፤ እንሸሽገው ዘንድ አንችልም፤