Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 105:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከአብርሃም ጋር ያደረገውን ኪዳን፥ ለይስሐቅም የማለውን፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከአብርሃም ጋራ የገባውን ቃል ኪዳን፣ ለይሥሐቅም የማለውን መሐላ አይረሳም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ይጠብቃል፤ ለይስሐቅ የሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የኤ​ር​ት​ራ​ንም ባሕር ገሠ​ጻት፥ ደረ​ቀ​ችም፤ እንደ ምድረ በዳ በጥ​ልቅ መራ​ቸው።

参见章节 复制




መዝሙር 105:9
13 交叉引用  

እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።


ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል አደርጋለሁ፥ እጅግም አበዛሃለሁ” አለው።


በዚህች ምድር ተቀመጥ፥ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፥ እባርክሃለሁም፥ እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህ ለአብርሃም የማልሁለትንም መሐላ አጸናለሁ።


እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ፦ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፥


እግዚአብሔርም አለው፦ “ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፥ ብዛ፥ ተባዛም፥ ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፥ ነገሥታትም ከጉልበትህ ይወጣሉ።


እግዚአብሔር ግን በቸርነቱ ምሕረትን በማድረግ ረዳቸው እንጂ እንዲደመሰሱ አልፈቀደም፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የሰጠውን ቃል ኪዳን በማሰብ ሕዝቡን ስላልረሳው ነው።


ልቡም በፊትህ ታማኝ ሆኖ አገኘኸው፥ የከነዓናዊውን፥ የኬጢያዊው፥ የአሞራዊውን፥ የፌርዛዊውን፥ የኢያቡሳዊውንና የጌርጌሳዊውን ምድር ለዘሩ ልትሰጥ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረግህ፥ አንተም ጻድቅ ነህና ቃልህን ፈጸምህ።”


እግዚአብሔርም የለቅሶአቸውን ድምፅ ሰማ፥ እግዚአብሔርም ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አስታወሰ።


ይህ ዛሬ እንደሆነ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለአባቶቻችሁ እንድሰጣቸው የማልሁትን መሐላ እንዳጸና ነው።” እኔም፦ “አቤቱ! አሜን” ብዬ መለስሁለት።


የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ እንዲሁም ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የአባቶችን አለቆች።


ይህንም እላለሁ፦ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የመጣው ሕግ፥ የተስፋውን ቃል ለማስቀረት፥ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን ሊሽር አይችልም።


ስለዚህም እግዚአብሔር የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደ ማይለወጥ አብልጦ ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ፥ በመሓላ በመካከል ገባ፤


跟着我们:

广告


广告