Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 101:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ባልንጀራውን በቀስታ የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፥ በዓይኑ ትዕቢተኛ፥ በልቡ ኩራተኛ የሆነውን አልታገሥም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ባልንጀራውን በስውር የሚያማውን፣ አጠፋዋለሁ፤ ትዕቢተኛ ዐይንና ኵራተኛ ልብ ያለውን፣ እርሱን አልታገሠውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሰውን በሹክሹክታ የሚያማውን ሰው ዝም አሰኛለሁ፤ ትዕቢተኛ ዐይንና ትምክሕተኛ ልብ ያለውን ሰው አልታገሠውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ከጩ​ኸቴ ድምፅ የተ​ነሣ ሥጋዬ በአ​ጥ​ን​ቶቼ ላይ ተጣ​በቀ።

参见章节 复制




መዝሙር 101:5
25 交叉引用  

ጌታ ከፍ ያለ ነውና፥ ዝቅተኞችን ይመለከታልና፥ ትዕቢተኞችን ግን ከሩቅ ያውቃል።


በአንደበቱ የማይሸነግል፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥ የሚቀርቡትን የማይሰድብ።


ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፥ ከጠማማም ጋር ብልህ ሆነህ ትገኛለህ።


ተቀምጠህ በወንድምህን ላይ ክፉን ተናገርህ፥ የእናትህንም ልጅ አማህ።


“በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።


“ሐሰተኛ ወሬ አታሰራጭ፥ ሐሰተኛ ምስክር ለመሆንም ከኃጢአተኛ ጋር አትተባበር።


ጥላቻን የሚከድን ሐሰተኛ ከንፈር አለው፥ ሐሜትንም የሚገልጥ አላዋቂ ነው።


ዘዋሪ ሐሜተኛ ምሥጢርን ይገልጣል፥ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ሰውን አትገናኘው።


ትዕቢተኛ ዓይንና ደፋር ልብ የኀጥኣንም እርሻ ኃጢአት ነው።


የሰሜን ነፋስ ዝናብ ያመጣል፥ ሐሜተኛ ምላስም የሰውን ፊት ያስቈጣል።


በትዕቢት ከፍ ከፍ ያሉ ዐይኖች ያሉት፥ ሽፋሽፍቶቹም ወደ ላይ የሚያዩ ትውልድ አለ።


የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤ የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤ በዚያን ቀን ጌታ ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።


ሐሜተኞች ሰዎች ደምን ሊያፈስሱ በአንቺ ውስጥ ነበሩ፥ በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ በሉ፥ በመካከልሽ ሴሰኝነትን አደረጉ።


በሕዝብህ መካከል በሸንጋይነት ወድያና ወዲህ አትመላለስ፤ በባልንጀራህም ሕይወት ላይ መሰነናክል ሆነህ አትቁም፤ እኔ ጌታ ነኝ።


ከዚያኛው ይልቅ ይህ ሰው ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ እላችኋለሁ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላልና፥ ራሱን ግን ዝቅ የሚያደርግ ከፍ ይላል።”


አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ስግብግብ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ።


እንዲሁም ሴቶች መልካም ሥነ ምግባር ያላቸው፥ ሐሜተኞች ያልሆኑ፥ በመጠን የሚኖሩ፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።


እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በመልካም ጠባያቸው የተቀደሱ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ ያልተገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ እንዲሆኑ ንገራቸው፤


እጅግ በመኩራራት አትናገሩ፥ የእብሪትም ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፥ ጌታ አምላክ አዋቂ ነውና፥ በእርሱም ሥራዎች ይመዘናሉ።


跟着我们:

广告


广告