Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መዝሙር 100:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የምስጋና መዝሙር። ምድር ሁሉ፥ ለጌታ እልል በሉ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በምድር ላይ የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ለእግዚአብሔር “እልል!” በሉ!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ንና ፍር​ድን እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ።

参见章节 复制




መዝሙር 100:1
18 交叉引用  

የዳዊት የምስጋና መዝሙር። አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥ ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም እባርካለሁ።


ጻድቃን ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ፥ ልባችሁም የቀና ሁላችሁ፥ እልል በሉ።


ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።


ለሚወደው ለያዕቆብ ኩራት የሆነችውን ርስታችንን እርሱ ይመርጥልናል።


ለመዘምራን አለቃ፥ የመነሣት የምስጋና መዝሙር።


በምድር ያሉ ሁሉ ለአንተ ይሰግዳሉ፥ ለአንተም ይዘምራሉ፥ ለስምህም ይዘምራሉ።”


አቤቱ፥ አሕዛብ ያመስግኑህ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ።


መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፥ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።


ምድር ሁሉ ሆይ፥ ለጌታ እልል በሉ፥ በደስታ ፈንድቁ፥ ዘምሩም።


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ዘምሪ፤ እስራኤል ሆይ፥ እልል በሉ፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ በፍጹም ልብሽ ሐሴት አድርጊ ደስም ይበልሽ።


ጌታም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያ ቀን ጌታ አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።


ወደ ደብረዘይት ቁልቁለትም ወዲያው በቀረበ ጊዜ፥ ደቀመዛሙርቱ በሙሉ ስላዩአቸው ተአምራት ደስ እያላቸው በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን ማመስገን ጀመሩ፤


እንደገናም “አሕዛብ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ፤” ይላል።


“የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላልና፥ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ ምድሪቱንና ሕዝቡን ይክሳልና፥ እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ።”


跟着我们:

广告


广告