ምሳሌ 6:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ስለዚህ ጥፋት ድንገት ይደርስበታል፥ ድንገት ይደቅቃል፥ ፈውስም ከቶ የለውም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ስለዚህ በቅጽበት መዓት ይወርድበታል፤ በድንገት ይጠፋል፤ መዳኛም የለውም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ስለዚህም በድንገት ጥፋት ይደርስበታል፤ ሊድን በማይችልበት ሁኔታ በቅጽበት ይወድማል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ስለዚህ የማይድን ውድቀትና መመታት፥ ጥፋትም ድንገት ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር በሚጠላቸው ሁሉ ደስ ይለዋልና፤ ስለ ነፍሱ ርኵሰትም ይደቅቃልና፥ 参见章节 |
መከራቸው ድንገት ይነሣልና፥ ከሁለቱ የሚመጣውን ጥፋት ማን ያውቃል? (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) የነገሩትን የሚሰማ ልጅ ከጥፋት የራቀ ነው፥ የነገሩትን የሚቀበልን ሰው እግዚአብሔር ይቀበለዋል። ከንጉሥ አንደበት ምንምን ሐሰት ይነገራል አይባልም፥ ከአንደበቱም የሚወጣ ሐሰት የለም። የንጉሥ ቃል ሾተል ናት፥ ለጥፋት የተሰጠችውን ሰው ሰውነት ታጠፋዋለች እንጂ አንድ አካል ብቻ የምታጠፋ አይደለም። ሰይፈ መዓቱ ብትሳል ግን ከወገኑ ጋር ሰውን ታጠፋለች፥ ከአሞሮች ግልገል ወገን የማይበላ እስኪሆን ድረስ እንደ እሳት ነበልባል ታቃጥላለች።