Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ትላለህም፦ “እንዴት ትምህርትን ጠላሁ፥ ልቤም ዘለፋን ናቀ!

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እንዲህም ትላለህ፤ “ምነው ተግሣጽን ጠላሁ! ልቤስ ምነው መታረምን ናቀ!

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እንዲህም ትላለህ፦ “የማልማረውና የሰውን ተግሣጽ የማልቀበለው ከቶ ለምንድን ነው!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እንዲህም ትላለህ፦ “እንዴት ትምህርትን ጠላሁ! ልቤም ከተግሣጽ እንዴት ራቀ!

参见章节 复制




ምሳሌ 5:12
23 交叉引用  

እነርሱም፦ “ወዲያ ሂድ” አሉት። ደግሞም እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው በእንግድነት ለመኖር መጣ፥ ፍርዱንም ይፈርድ ዘንድ ይፈልጋል፥ አሁን በአንተ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግብሃለን።” ሎጥንም እጅግ ተጋፉት፥ የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ።


እርሱም እየተናረ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው፦ “በውኑ አንተ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሾመነሃልን? ተው፤ እንዲገድሉህ ለምን ትሻለህ?” ነቢዩም፦ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና ጌታ ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ተወ።


እነርሱ ግን የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በጌታ መልክተኞች ይሳለቁ፥ ቃላቱንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።


አንተስ ተግሣጼን ጠላህ፥ ቃሎቼንም ወደ ኋላህ ጣልህ።


እኔ የተናቅሁ ነኝ አላወቅሁምም፥ በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ።


“እናንት አላዋቂዎች፥ እስከ መቼ አላዋቂነት ትወድዳላችሁ? ፌዘኞችም ፌዝን ይፈቅዳሉ? ሞኞችም እውቀትን ይጠላሉ?


ምክሬን ሁሉ ግን ችላ ስላላችሁ፥ ዘለፋዬንም ስላልተቀበላችሁ፥


የዕውቀት መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥ ሞኞች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።


ተግሣጽን የሚጠብቅ በሕይወት መንገድ ይሄዳል፥ ዘለፋን የሚተው ግን ይስታል።


ተግሣጽን የሚወድድ እውቀትን ይወድዳል፥ እርማትን የሚጠላ ግን ሞኝ ነው።


ድህነትና ነውር ተግሣጽን ቸል ለሚሉ ነው፥ ዘለፋን የሚሰማ ግን ይከብራል።


ሰነፍ የአባቱን ተግሣጽ ይንቃል፥ ዘለፋን የሚቀበል ግን አእምሮው የበዛ ነው።


በመጨረሻም ሥጋህና ሰውነትህ በጠፋ ጊዜ ታለቅሳለህ፥


ትእዛዝ መብራት፥ ትምህርትም ብርሃን ነውና፥ የተግሣጽም ዘለፋ የሕይወት መንገድ ነውና፥


እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጐዳል፥ የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወድዳሉ።”


ሆኖም በማለዳ ተነሥቼ ባርያዎቼን ነቢያትን ሁሉ እንዲህ ብዬ ላክሁባችሁ፦ ‘እባካችሁ፥ እንደዚህ ያለ የጠላሁትን ርኩስ ነገር አታድርጉ።’


跟着我们:

广告


广告