Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 13:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፥ አንዳችም አታገኝም፥ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሰነፍ አጥብቆ ይመኛል፤ አንዳችም አያገኝም፤ የትጉሆች ምኞት ግን ይረካል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሰነፍ አንድ ነገር ለማግኘት አጥብቆ ይመኛል፤ ይሁን እንጂ አያገኝም፤ ትጉህ ሠራተኛ ግን የሚፈልገውን ሁሉ ያገኛል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የማይሠራ ሁሉ በምኞት ይኖራል። የደጋጎች እጅ ግን ይተጋል።

参见章节 复制




ምሳሌ 13:4
26 交叉引用  

በዚያም ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጡ፥ ስለ ቈፈሩአትም ጉድጓድ፦ “ውኃ አገኘን ብለው ነገሩት።”


በጌታ ቤት ውስጥ ተተክለዋል፥ በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ።


የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፥ የትጉ እጅ ግን ሀብታም ታደርጋለች።


በረከትን የምታካፍል ነፍስ ትጠግባለች፥ ውሃን የሚያጠጣ እርሱ ደግሞ ይረካል።


መሬቱን የሚቆፍር ሰው እንጀራ ይጠግባል፥ ለከንቱ ነገር የሚሮጥ ግን ማስተዋል የተሣነው ነው።


የትጉ እጅ ትገዛለች፥ የታካች እጅ ግን ትገብራለች።


ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም፥ ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው።


አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፥ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋት ያገኘዋል።


ጻድቅ ሐሰትን ይጠላል፥ ኀጥእ ግን ያሳፍራል ያስነውራልም።


ታካች ሰው በብርድ ምክንያት አያርስም፥ ስለዚህ በመከር ይለምናል፥ ምንም አያገኝም።


ታካችን ምኞቱ ትገድለዋለች፥ እጆቹ ይሠሩ ዘንድ አይፈቅዱምና።


የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፥ ችኩል ሰው ግን ለመጉደል ይቸኩላል።


በሰነፍ ሰው እርሻ፥ አእምሮ በጐደለውም ሰው ወይን ቦታ አለፍሁ።


እነሆም፥ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፥ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል፥ የድንጋዩም ቅጥር ፈርሶአል።


ሰነፍ ሰው፦ “አንበሳ በመንገድ ላይ አለ፥ አንበሳ በጎዳናዎች ላይ አለ” ይላል።


ስግብግብ ሰው ክርክርን ያነሣሣል፥ በጌታ የሚታመን ግን ይጠግባል።


አንተ ሰነፍ፥ ወደ ገብረ ጉንዳን ሂድ፥ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን።


የሚሰማኝ ሰው ምስጉን ነው ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥ የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ።


ቀሚሴን አወለቅሁ፥ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ፥ እንዴት አሳድፈዋለሁ?


ጌታም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።


የያዕቆብን ትቢያ ማን ይቈጥራል? የእስራኤልስ አራተኛውን ክፍል ማን ይቈጥራል? የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።”


ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”


እናንተም ሁላችሁ በተስፋ የምትጠባበቁትን ነገር እስክትጨብጡ ድረስ ትጋታችሁን እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን፤


ወደ ኢያሱም ተመልሰው እንዲህ አሉት፦ “ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰው ወጥተው ጋይን ይምቱ እንጂ ሕዝቡ ሁሉ አይውጣ፤ ጥቂቶች ናቸውና ሕዝቡ ሁሉ ወደዚያ ለመሄድ አይድከም።”


跟着我们:

广告


广告