Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 13:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ጻድቅ ሰውነቱ እስክትጠግብ ድረስ ይበላል፥ የኀጥኣን ሆድ ግን ይራባል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ጻድቅ እስኪጠግብ ድረስ ይበላል፤ የክፉዎች ሆድ ግን እንደ ተራበ ይኖራል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እውነተኞች ሊበሉ የሚፈልጉትን ያኽል ያገኛሉ። ኃጢአተኞች ግን ዘወትር ይራባሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ጻድቅ ሰውነቱ እስክትጠግብ ድረስ ይበላል፤ የኃጥኣን ሰውነት ግን ትቸገራለች።

参见章节 复制




ምሳሌ 13:25
17 交叉引用  

ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጎልማሳነትሽን እንደ ንስር ያድሳል።


ስንቆቿን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ።


የሚፈሩት ምንም አያጡምና ቅዱሳኑ ሁሉ፥ ጌታን ፍሩት።


በጻድቅ ዘንድ ያለው ጥቂት ነገር ከብዙ ክፉዎች ሀብት ይበልጣል።


በጌታ ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።


ጌታ የጻድቁን ነፍስ አያስርብም፥ የክፉዎችን ምኞት ግን ይገለብጣል።


ድህነትና ነውር ተግሣጽን ቸል ለሚሉ ነው፥ ዘለፋን የሚሰማ ግን ይከብራል።


እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥ ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል። (በግዕዝ መጽሐፈ ተግሣጽ ይባላል)።


እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥ ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።


ሁሉንም ከከሰረ በኋላ በዚያች አገር ጽኑ ራብ ሆነ፤ እርሱም ይጨነቅ ጀመር።


ጌታ የሚያስነሣብህን ጠላቶችህን ታገለግላለህ፤ በራብና በጥማት፥ በእርዛትና በማጣት እስኪያጠፉህም ድረስ በዐንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭኑብሃል።


በሚያቃጥል ንዳድና በራብ ያልቃሉ፤ በወረርሽኝ መቅሠፍት ይጠፋሉ፤ ተናካሽ አውሬዎችን፥ ከሚሳቡ መርዘኛ እባቦችን ጋር እሰድባቸዋለሁ።


እንዲሁም ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “ማንም ሊሠራ የማይወድ አይብላ፤” ብለን አዘናችሁ ነበር።


ሰውነትን አካላዊ እንቅስቃሴ ማለማመድ መጠነኛ ጠቀሜታ ቢኖረውም እንኳ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣውን ሕይወት የተስፋ ቃል ስላለው፥ ለሁሉ ነገር ይጠቅማል።


ሕይወታችሁ ከፍቅረ ንዋይ የጸዳ ይሁን፤ ነገር ግን እርሱ ራሱ “አልለቅህም፤ ከቶም አልተውህም፤” ብሎአልና ያላችሁ ይብቃችሁ።


跟着我们:

广告


广告