Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 13:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፥ ልጁን የሚወድድ ግን ተግቶ ይገሥጸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በአርጩሜ ከመቅጣት የሚሳሳለት ልጁን ይጠላል፤ የሚወድደው ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ልጁን የማይቀጣ አይወደውም ማለት ነው፤ ልጁን የሚወድ ግን ቀጥቶ ያሳድገዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፤ ልጁን የሚወድድ ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል።

参见章节 复制




ምሳሌ 13:24
10 交叉引用  

ተስፋ ገና ሳለች ልጅህን ገሥጽ፥ መሞቱንም አትሻ።


ቂልነት በልጅ ልብ ውስጥ ተተብትቧል፥ የተግሣጽ በትር ግን ነፃ ያደርገዋል።


በትርና ተግሣጽ ጥበብን ይሰጣሉ፥ ያልተቀጣ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።


ልጅህን ቅጣ ዕረፍትንም ይሰጥሃል፥ ለነፍስህም ደስታን ይሰጣታል።


ጌታ የወደደውን ይገሥጻልና፥ አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ።


እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጐዳል፥ የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወድዳሉ።”


“ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት እንኳን ሳይቀር ካልናቀ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።


እንግዲህ ሰው ልጁን እንደሚገሥፅ፥ እንዲሁም ጌታ እግዚአብሔር አንተን እንደሚገሥጽህ በልብህ አስተውል።


跟着我们:

广告


广告