Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 13:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የተፈጸመች ፈቃድ ሰውነትን ደስ ታሰኛለች፥ ሰነፎች ግን ከክፉ መራቅን ይጸየፋሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ምኞት ስትፈጸም ነፍስን ደስ ታሰኛለች፤ ሞኞች ግን ከክፋት መራቅን ይጸየፋሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የተመኙትን ነገር ማግኘት እጅግ ደስ ያሰኛል፤ ማስተዋል የጐደላቸው ሰዎች ግን ከክፉ ነገር መራቅ አይፈልጉም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የደጋግ ሰዎች ምኞት ነፍስን ያድናል፤ የሰነፎች ሥራ ግን ከዕውቀት የራቀ ነው።

参见章节 复制




ምሳሌ 13:19
17 交叉引用  

ንጉሡም ደግሞ፦ ‘ዓይኔ እያየ ዛሬ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጠውን የሰጠኝ የእስራኤል አምላክ ጌታ ይመስገን!’ አለ።”


ሰውንም፦ ‘እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፥ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው’ አለው።”


አንደበትህን ከክፉ ነገር፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን ከመናገር ከልክል።


ከክፉ ሽሽ፥ መልካምንም አድርግ፥ ለዘለዓለምም ትኖራለህ።


የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች፥ የተገኘች ፈቃድ ግን የሕይወት ዛፍ ናት።


ድህነትና ነውር ተግሣጽን ቸል ለሚሉ ነው፥ ዘለፋን የሚሰማ ግን ይከብራል።


ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፥ የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።


የቅኖች መንገድ ከክፋት መራቅ ነው፥ መንገዱን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃታል።


በምሕረትና በእውነት ኃጢአት ትሰረያለች፥ ጌታንም በመፍራት ሰው ከክፋት ይመለሳል።


ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ንጹሑን ሰው ይጠላሉ፥ እንዲሁም የቅኑን ሰው ነፍስ ይሻሉ።


ኃጢአተኛ በጻድቃን ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ በቀና መንገድ የሚሄደውም በኀጥኣን ዘንድ አስጸያፊ ነው።


በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፥ ጌታን ፍራ፥ ከክፋትም ራቅ፥


ከእነርሱም ጥቂት እልፍ ብዬ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት፥ ያዝሁትም ወደ እናቴም ቤት ወደ ወለደችኝም እልፍኝ እስካገባው ድረስ አልተውሁትም።


ሆኖም የእግዚአብሔር ጠንካራ መሠረት የቆመው፦ “ጌታ የራሱ የሆኑትን ያውቃል፤” እንዲሁም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለውን ማኅተም ታትሞ ነው።


跟着我们:

广告


广告