Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 12:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ጻድቅን መከራ አያገኘውም፥ ኀጥኣን ግን ክፋትን የተሞሉ ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ጻድቃን ጕዳት አያገኛቸውም፤ ክፉዎች ግን በመከራ የተሞሉ ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ደጋግ ሰዎች ምንም ክፉ ነገር አይገጥማቸውም፤ ክፉዎች ግን መከራ ይበዛባቸዋል። የሚያተርፉት ነገር የለም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ጻድቅን ምንም ክፉ ነገር ደስ አያሰኘውም፤ ክፉዎች ግን ክፋትን የተሞሉ ናቸው።

参见章节 复制




ምሳሌ 12:21
17 交叉引用  

ጌታ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል።


ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።


ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ የገዛ ራሳቸውን ምክር ይጠግባሉ።


የሚሰማኝ ግን ተረጋግቶ ይቀመጣል፥ ከክፉም ሥጋት ያርፋል።”


ክፉ ሰው በእርግጠኛነት ሳይቀጣ አይቀርም፥ የጻድቃን ዘር ግን ይድናል።


ክፉን በሚያስቡ ልብ ውስጥ ተንኰል አለ፥ በሰላም ለሚመክሩ ግን ደስታ አላቸው።


ልቡን ከጽድቅ የሚመልስ ሰው ከመንገዱ ፍሬ ይጠግባል፥ ጻድቅም ሰው ደግሞ በራሱ።


ጌታን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፥ የሚፈራውም ጠግቦ ይኖራል፥ ክፉ ነገርም አያገኘውም።


እግዚአብሔርን የሚፈራ በሁሉም ይዋጣለታልና ይህን ብትይዝ፥ ከዚያም ደግሞ እጅህን ባታርቅ መልካም ነው።


ትእዛዝን የሚጠብቅ ክፉ ነገር አይገጥመውም፥ የጠቢብም ልብ ጊዜንና ፍርድን ያውቃል።


በክብር ፈንታ እፍረት ሞልቶብሃል፤ አንተ ደግሞ ጠጣ፥ እንዳልተገረዘም ተቆጠር፤ የጌታ የቀኙ ጽዋ በአንተ ላይ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል።


እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ ዓላማውም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።


ቀላል የሆነው ጊዜያዊ መከራችን ከመመዘኛዎች ሁሉ ለሚያልፈው ለዘላለማዊ ክብር ያዘጋጀናል።


ለመልካም ነገር ቀናኢ ብትሆኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው?


እርሷ በሰጠችው መጠን መልሱላት፤ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤


跟着我们:

广告


广告