Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 10:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በብልሃተኛ ከንፈር ጥበብ ትገኛለች፥ በትር ግን አእምሮ ለጐደለው ሰው ጀርባ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ጥበብ በአስተዋይ ሰው ከንፈር ትገኛለች፤ በትር ግን ለልበ ቢስ ሰው ጀርባ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በአእምሮ የበሰሉ ሰዎች በማስተዋል ይናገራሉ። ሞኞች ግን ቅጣት መቀበል የሚገባቸው ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ብልህ ሰው ከከንፈሩ ጥበብን ያወጣል፤ አእምሮ የጐደለውንም ሰው በበትር ይመታል።

参见章节 复制




ምሳሌ 10:13
18 交叉引用  

ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጉሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።


የጻድቅ አፍ ጥበብን ያናገራል፥ አንደበቱም ፍርድን ይናገራል።


ጌታም ሙሴን፦ “አንበጣዎቹ በግብጽ ምድር ላይ እንዲመጡ፥ ከበረዶውም የተረፈውን የምድርን ቡቃያ ሁሉ እንዲበሉ፥ እጅህን በግብጽ ምድር ላይ ዘርጋ” አለው።


የጻድቅ ከንፈሮች ብዙ ሰዎችን ይመግባሉ፥ አላዋቂዎች ግን ከማስተዋል ጉድለት የተነሣ ይሞታሉ።


የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፥ የመጥመም ምላስ ግን ትቈረጣለች።


ሰው በአፉ መልስ ደስ ይለዋል፥ ቃልም በጊዜው ምንኛ መልካም ነው!


የጠቢባን ከንፈር እውቀትን ትዘራለች፥ የሰነፎች ልብ ግን እንዲህ አይደለም።


ልቡ ጠቢብ የሆነ አስተዋይ ይባላል፥ በከንፈሩም ጣፋጭ የሆነ ትምህርትን ያበዛል።


መቶ ግርፋት በሰነፍ ጠልቆ ከሚገባ ይልቅ ተግሣጽ በአስተዋይ ሰው ጠልቆ ወደ ልቡ ይገባል።


ለሚያፌዙ ሰዎች ፍርድ ተዘጋጅታለች፥ ለሰነፎችም ጀርባ በትር።


ወርቅና ብዙ ቀይ ዕንቁ ይገኛል፥ የእውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።


አለንጋ ለፈረስ፥ ልጓም ለአህያ፥ በትርም ለሞኝ ጀርባ ነው።


ሰነፍን በሙቀጫ ውስጥ ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠው፥ ሞኝነቱ ከእርሱ አይርቅም።


ከሴት ጋር የሚያመነዝር ግን አእምሮ የጐደለው ነው፥ እንዲሁም የሚያደርግ ነፍሱን ያጠፋል።


እርሱ እንዲህ ስቶ ይከተላታል፥ በሬ ለመታረድ እንደሚነዳ፥ አጋዘን ቸኩሎ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ፥


የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ እንዳውቅ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም እንድትሰማ ጆሮዬን ያነቃቃል።


ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር፤ ከአፉም ከሚወጡት ቃላት ጸጋ የተነሣ እየተደነቁ፦ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።


跟着我们:

广告


广告