Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 6:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አንድ ሌማትም እርሾ ያልገባበት እንጀራ፥ በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄትም የተሠሩ እንጐቻዎች፥ በዘይትም የተቀባ እርሾ ያልገባበት ስስ ቂጣ፥ የእህሉንም ቁርባን፥ የመጠጡንም ቁርባን ያቅርብ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከእነዚህም ጋራ የሚቀርበውን የእህልና የመጠጥ ቍርባን ቂጣ ማለት ከላመ ዱቄት በዘይት የተለወሱ ዕንጐቻዎች እንዲሁም በሥሡ የተጋገረና ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ ያምጣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ደግሞም እርሾ ሳይነካው የተጋገረ አንድ መሶብ እንጀራ፥ በወይራ ዘይት ከተለወሰ ዱቄት የተጋገረ ውፍረት ያለው ኅብስት፥ በወይራ ዘይት የተቀቡ ስስ ቂጣዎች ጭምር ከሚቀርበው ከእህል ቊርባንና ከመጠጥ መባ ጋር አብሮ ይቅረብ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አንድ ሌማ​ትም በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የስ​ንዴ ቂጣ እን​ጀራ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ቀባ ስስ ቂጣ፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን ያቅ​ርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አንድ ሌማትም ቂጣ እንጀራ፥ በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄትም የተሠሩ እንጐቻዎች፥ በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ፥ የእህሉንም ቍርባን፥ የመጠጡንም ቍርባን ያቅርብ።

参见章节 复制




ዘኍል 6:15
15 交叉引用  

ያልቦካ ቂጣ፥ በዘይት የተለወሰ ያልቦካ እንጎቻ፥ በዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ፥ ከመልካም ስንዴ አዘጋጅ።


ነገር ግን የሰበሰቡት ይበሉታል ጌታንም ያመሰግናሉ፥ ያከማቹትም በመቅደሴ አደባባይ ላይ ይጠጡታል ብሎ በቀኙና በኃይሉ ክንድ ምሏል።


የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት፥ ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የመሠዊያ አገልጋዮች፥ ዋይ በሉ፥ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች፥ ኑ፥ ሌሊቱን ሁሉ በማቅ ላይ ተኙ።


የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከጌታ ቤት ተወግዶአል፥ የጌታ አገልጋዮች ካህናቱ አለቀሱ።


የሚመለስና የሚጸጸት እንደሆነ፥ ጌታ አምላካችሁም የእህልና የመጠጥ ቁርባን የሚሆነውን በረከት የሚያተርፍ እንደሆነ ማን ያውቃል?


“በምድጃ የተጋገረውን የእህል ቁርባን ስታቀርብ በዘይት ተለውሶ እርሾ ያልገባበት፥ የመልካም ዱቄት የቂጣ እንጐቻ ወይም እርሾ ያልነካው በዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ ይሁን።


የሚያቀርውም ለምስጋና ቢሆን፥ ከምስጋናው መሥዋዕት ጋር እርሾ ያልገባበት በዘይት የተለወሰ የቂጣ እንጎቻ፥ እርሾ ያልነካው በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘይትም የተለወሰ መልካም ዱቄት ያቀርባል።


“አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅባቱንም ዘይት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትም የሚቀርበውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ እርሾ ያልነካው ቂጣ የሚቀመጥበትንም መሶብ ውሰድ፤


ለአንድነትም መሥዋዕት በሬንና አውራን በግ፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቁርባን በጌታ ፊት ለመሠዋት ውሰዱ፥ ዛሬ ጌታ ተገልጦላችኋልና።’ ”


ለጌታም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርገህ፥ የኢን መስፈሪያ ግማሽ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን ታቀርባለህ።


ካህኑም በጌታ ፊት ያቀርባቸዋል፥ የኃጢአቱንም መሥዋዕት የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ያሳርግለታል።


እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማናቸውንም ነገር ስታደርጉ፥ ሁሉን ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።


ይህን ኅብስት በምትበሉበትና ይህንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ።


跟着我们:

广告


广告