Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 31:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም የማኅበሩም አለቆች ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ ሊገናኙአቸው ወጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሙሴ፣ ካህኑ አልዓዛርና የማኅበረ ሰቡ መሪዎች በሙሉ ሊቀበሏቸው ከሰፈር ወጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሙሴ፥ አልዓዛርና ሌሎቹም የማኅበሩ መሪዎች ሠራዊቱን ለመቀበል ከሰፈር ወጡ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም፥ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ሊገ​ና​ኙ​አ​ቸው ወጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም የማኅበሩም አለቆች ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ ሊገናኙአቸው ወጡ።

参见章节 复制




ዘኍል 31:13
9 交叉引用  

ኮሎዶጎምርንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ወግቶ ከተመለሰ በኋላም የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሸለቆ በሆነ በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ።


“አንድ ገዢም ኃጢአትን ቢሠራ፥ ጌታም አምላኩ አትሥራ ያለውን ትእዛዝ አንዱን ባለማወቅ ሠርቶ ቢበድል፥


“የሞተውን የማናቸውንም ሰው በድን የሚነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፤


የማረኩአቸውንም ሰዎች ምርኮውንና ብዝበዛውን፥ በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ወዳለው ሰፈር፥ ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር አመጡ።


ሙሴም ከዘመቻ በተመለሱት በጦሩ አዛዦች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ።


“የእስራኤል ልጆች የለምጽ ደዌ ያለበትን ሁሉ፥ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ፥ ሬሳንም በመንካት የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤


ሳሙኤልም ጠዋት ተነሥቶ በማለዳ ሳኦልን ለመገናኘት ሄደ፤ ነገር ግን፥ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ ሄዷል፤ ለራሱ ክብር የመታሰቢያ ሐውልት በዚያ ካቆመ በኋላ ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወርዷል” ተብሎ ተነገረው።


ከዚያም ዳዊት እጅግ በመድከማቸው ምክንያት ሊከተሉት ወዳልቻሉት በብሦር ወንዝ ቀርተው ወደነበሩት ወደ ሁለቱ መቶ ሰዎች መጣ፤ እነርሱም ዳዊትንና አብረውት የነበሩትን ሰዎች ለመቀበል ወጡ። ዳዊትና ሰዎቹ ወደ እነርሱ እንደ ቀረቡም ዳዊት ሰላምታ ሰጣቸው።


跟着我们:

广告


广告