Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 30:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ባልዋም ቢሰማ፥ በሰማበትም ቀን ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ይጸናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ባሏም ሰምቶ ምንም ነገር ሳይላት ቢቀር ስእለቶቿ ወይም ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸው ነገሮች መፈጸም ይኖርባቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ባልዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ካልከለከላት በቀር ስእለትዋንም ሆነ የገባችውን ቃል መፈጸም አለባት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ባል​ዋም ቢሰማ፥ በሰ​ማ​በ​ትም ቀን ዝም ቢላት፥ ስእ​ለቷ፥ ራስ​ዋ​ንም ያሰ​ረ​ች​በት መሐላ ይጸ​ናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ባልዋም ቢሰማ፥ በሰማበትም ቀን ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ይጸናል።

参见章节 复制




ዘኍል 30:7
7 交叉引用  

ለሴቲቱም አላት፥ “በእርግዝናሽ ወራት ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፥ በጭንቅ ትወልጃለሽ፥ ይህም ሁሉ ሆኖ ፍላጎትሽ ለባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።”


እኛስ ለሰማይ ንግሥት ባጠንንላት የመጠጥንም ቁርባን ባፈሰስንላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎቻችን ፈቃድ ምስልዋ ያለበት እንጐቻ አድርገንላታልን? የመጠጥንስ ቁርባን አፍስሰንላታልን?”


“ስእለትም ከተሳለች ወይም ራስዋን በመሐላ ያሰረችበትን ነገር ከአንደበትዋ በችኮላ ከተናገረች በኋላ ባል ብታገባ፥


ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ በእርሷ ላይ ያለውን ስእለትዋን ከአንደበትዋም በችኮላ ተናግራ ራስዋን በመሐላ ያሰረችበትን ነገር ከንቱ ያደርገዋል፤ ጌታም ይቅር ይላታል።


ያገባች ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ በሕግ ታስራለችና፤ ባሏ ቢሞት ግን ከባል ሕግ ተፈትታለች።


እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሠራዊት ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለአገልጋይህም ወንድ ልጅ ብትሰጣት፥ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለጌታ እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አያርፍም።”


ባሏ ሕልቃናም፥ “መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ፤ ጡት እስክታስጥይው ድረስ እዚሁ ቆይ፤ ብቻ ጌታ ቃሉን ያጽናልሽ” አላት። ስለዚህ ሴቲቱ ሕፃኑን ጡት እስክታስጥለው ድረስ እያጠባችው በቤቷ ተቀመጠች።


跟着我们:

广告


广告