Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 30:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ዳሩ ግን ነገሩን ከሰማ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከንቱ ቢያደርገው በደልዋን ይሸከማል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለ ነገሮቹ ከሰማ በኋላ እንዲቀሩ ካደረገ ግን ለፈጸመችው በደል በኀላፊነት የሚጠየቀው ራሱ ነው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ነገር ግን ቈየት ብሎ ስእለቱን የሚቃወም ከሆነ ለስእለቱ አለመፈጸም ኀላፊ ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከሰ​ማው በኋላ ግን ቢከ​ለ​ክ​ላት ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከሰማው በኋላ ግን ከንቱ ቢያደርገው ኃጢአትዋን ይሸከማል።

参见章节 复制




ዘኍል 30:15
7 交叉引用  

“ማንም ሰው የመሓላን ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ ወይም ስለ ነገሩ አይቶ ወይም አውቆ ባይናገር፥ ኃጢአት መሥራቱ ነውና በደሉን ይሸከማል።


ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ከንቱ ቢያደርገው፥ ስለ ስእለትዋ ወይም ራስዋን ስላሰረችበት መሐላ በአንደበትዋ የተናገረችው ማናቸውም ነገር አይጸናም፤ ባልዋ ከንቱ አድርጎታል፤ ጌታም ይቅር ይላታል።


ባልዋ ግን በየዕለቱ ዝም ቢላት፥ ስእለትዋን ሁሉ በእርሷም ላይ ያለውን መሐላ ሁሉ አጽንቶታል፤ በሰማበት ቀን ዝም ብሎአታልና አጽንቶታል።


እርሷ በብላቴንነትዋ ጊዜ በአባትዋ ቤት ሳለች በአባትና በልጂቱ መካከል፥ ወይም በባልና በሚስት መካከል እንዲሆን ጌታ ሙሴን ያዘዘው ሥርዓት ይህ ነው።”


አባትዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለትዋ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላዋ አይጸኑም፤ አባትዋ ከልክሎአታልና ጌታ ይቅር ይላታል።


ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ በእርሷ ላይ ያለውን ስእለትዋን ከአንደበትዋም በችኮላ ተናግራ ራስዋን በመሐላ ያሰረችበትን ነገር ከንቱ ያደርገዋል፤ ጌታም ይቅር ይላታል።


በክርስቶስ ኢየሱስ ሁላችሁም አንድ ናችሁና አይሁዳዊ ወይም ግሪካዊ የለም፥ ባርያ ወይም ነጻ ሰው የለም፥ ወንድ ወይም ሴት የለም።


跟着我们:

广告


广告