Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 3:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 “ሌዋውያንን በእስራኤል ልጆች በኩር ሁሉ ፋንታ፥ የሌዋውያንንም እንስሶች በእንስሶቻቸው ፋንታ ውሰድ፤ ሌዋውያንም የእኔ ናቸው፤ እኔ ጌታ ነኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 “በእስራኤላውያን በኵሮች ምትክ ሌዋውያኑን፣ በከብቶቻቸውም ምትክ የሌዋውያኑን ከብቶች ውሰድ፤ ሌዋውያኑም የእኔ ይሁኑ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 “እንግዲህ በኲር ሆነው በሚወለዱት እስራኤላውያን ወንዶች ልጆች ምትክ ሌዋውያንን ለእኔ ለይልኝ፤ እንዲሁም በኲር ሆነው በሚወለዱት የእስራኤላውያን እንስሶች ምትክ የሌዋውያንን እንስሳት ለእኔ የተለዩ እንዲሆኑ አድርግ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 “ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌ​ዋ​ው​ያ​ን​ንም እን​ስ​ሶች በእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው ፋንታ ውሰድ፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም ለእኔ ይሁኑ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 ሌዋውያንን በእስራኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌዋውያንንም እንስሶች በእንስሶቻቸው ፋንታ ውሰድ፤ ሌዋውያንም ለእኔ ይሁኑ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

参见章节 复制




ዘኍል 3:45
7 交叉引用  

የአህያውን በኩር በጠቦት ትዋጀዋለህ፥ ካልዋጀኸው ግን አንገቱን ትሰብረዋለህ። የልጆችህንም በኩር ሁሉ ትዋጃለህ። በፊቴ አንድ ሰው ባዶ እጁን አይታይ።


ቃል ኪዳኔ ከሌዊ ጋር ለማድረግ ይህን ትእዛዝ እንደ ላክሁላችሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


እኔም፥ እነሆ፥ ሌዋውያንን ወንድሞቻችሁን ከእስራኤል ልጆች መካከል ወስጄአለሁ፤ የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት እንዲሠሩ ለጌታ የተሰጡ ለእናንተ ስጦታ ናቸው።


“እነሆ፥ እኔ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ማኅፀን በሚከፍተው በበኩሩ ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ወስጄአለሁ፤ ሌዋውያንም የእኔ ናቸው፥


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


እነርሱም ከእስራኤል ልጆች መካከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰጥተዋልና፤ በእስራኤል ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ማኅፀን በሚከፍተው ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስጄአቸዋለሁ።


跟着我们:

广告


广告