Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 29:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በዚህም በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ ራሳችሁንም አዋርዱ፤ ምንም ዓይነት ሥራ አትሥሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ ‘በዚሁ በሰባተኛው ወር በዐሥረኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ ራሳችሁን አዋርዱ፤ ሥራም አትሥሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን ለማምለክ ትሰበሰባላችሁ፤ በዚያን ቀን ምግብ አትመገቡም፤ ሥራም አትሠሩም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “የዚ​ህም ወር ዐሥ​ረ​ኛዋ ቀን ለእ​ና​ንተ የተ​ቀ​ደ​ሰች ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አስ​ጨ​ን​ቁ​አት፤ ከሥራ ሁሉ ምንም አታ​ድ​ርጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከዚህም ከሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ ሰውነታችሁን አስጨንቁት፤ ከሥራ ሁሉ ምንም አታድርጉ።

参见章节 复制




ዘኍል 29:7
17 交叉引用  

በአምላካችን ፊት ራሳችንን ዝቅ እንድናደርግ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንድንለምን በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ።


እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፥ ነፍሴንም በጾም አደከምኋት፥ ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ።


በዚያም ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ ልቅሶና ወደ ዋይታ፥ ጠጉራችሁን ወደ መንጨትና ማቅንም ወደ መልበስ ጠራችሁ።


በዳዊት ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የምሕረትንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ። እነርሱም ወደ እርሱ በሚመለከቱበት ጊዜ የወጉትን ይመለከታሉ። ሰውም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


ለሠራዊት ጌታ ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ “ለብዙ ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መጾምና ማልቀስ ይገባኛልን?” ብለው እንዲናገሩ ልኳቸው ነበር።


የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤ መፅናናትን ያገኛሉና።


“አይደለም”፤ እላችኋለሁ፥ “ነገር ግን ንስሓ ባትገቡ ሁላችሁም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።


ነገር ግን ንስሓ ባትገቡ ሁላችሁም እንደዚሁ ትጠፋላችሁ።”


ብዙ ጊዜም ካለፈ በኋላ፥ የፆም ወራት አሁን አልፎ ስለ ነበረ በመርከብ ለመሄድ አሁን የሚያስፈራ ነበርና ጳውሎስ


ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት ባርያዎች እንዳንሆን የኃጢአት ሰውነት እንዲሻር አሮጌው ማንነታችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን።


ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የቀረሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ።


跟着我们:

广告


广告