Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 22:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አህያይቱም የጌታን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤ እርሷም ከመንገዱ ፈቀቅ ብላ ወደ እርሻው ውስጥ ገባች፤ በለዓምም ወደ መንገድ እንድትመለስ አህያይቱን መታት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አህያዪቱም የእግዚአብሔር መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ በመንገድ ላይ መቆሙን ባየች ጊዜ ከመንገድ ወጥታ ዕርሻ ውስጥ ገባች፤ በለዓምም ወደ መንገዱ እንድትመለስ መታት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 መልአኩ ሰይፉን መዞ በመንገዱ ላይ መቆሙን አህያይቱ በተመለከተች ጊዜ መንገዱን ለቃ ወደ እርሻ ገባች፤ በለዓምም አህያይቱን ወደ መንገዱ ለመመለስ ደበደባት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እር​ሱም በአ​ህ​ያ​ዪቱ ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ሁለ​ቱም ብላ​ቴ​ና​ዎቹ ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ። አህ​ያ​ዪ​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ በመ​ን​ገድ ላይ ቆሞ የተ​መ​ዘ​ዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤ ከመ​ን​ገ​ዱም ላይ ፈቀቅ ብላ ወደ ሜዳ ውስጥ ገባች፤ በለ​ዓ​ምም ወደ መን​ገድ ይመ​ል​ሳት ዘንድ አህ​ያ​ዪ​ቱን መታት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አህያይቱም የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤ ከመንገዱም ፈቀቅ ብላ ወደ እርሻው ውስጥ ገባች፤ በለዓምም ወደ መንገድ ይመልሳት ዘንድ አህያይቱን መታት።

参见章节 复制




ዘኍል 22:23
11 交叉引用  

ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! ማየት እንዲችል ዐይኖቹን ክፈትለት!” ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕ አገልጋይ ዐይኖቹ እንዲከፈቱለት ስላደረገ፥ በኰረብታው ጐን ብዙ የእሳት ፈረሶችና ሠረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተሰልፈው የሚጠብቁት መሆናቸውን ተመለከተ።


ዳዊትም ዐይኖቹን አነሣ፤ የጌታ መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ። ዳዊትም ሽማግሌዎችም ማቅ ለብሰው በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።


እንዲሁም ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም የመምጫቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የጌታን ፍርድ አላወቁም።


እርሱም ስለ ሄደ እግዚአብሔር ተቈጣ፤ የጌታም መልአክ ሊቃወመው በመንገድ ላይ ቆመ። እርሱም በአህያይቱ ላይ ሆኖ ይጓዝ ነበር፥ ሁለቱም ሎሌዎቹ ከእርሱ ጋር ነበሩ።


የጌታም መልአክ ከወይኑ ቦታዎች መካከል በወዲያና በወዲህ ወገን ግንብ በነበረበት በጠባብ መንገድ ላይ ቆመ።


ከእኔ ጋር የነበሩትም ብርሃኑን አይተው ፈሩ፤ የሚናገረኝን የእርሱን ድምፅ ግን አልሰሙም።


እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ “አንተ ከእኛ ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን?” አለው።


ነገር ግን በለዓም ስለ መተላለፉ ተገሥጿአል፤ መናገር የማይችለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩን እብደት አገደ።


ወዮላቸው! በቃየል መንገድ ሄደዋልና፥ ለደመወዝ ብለው ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል፥ በቆሬም ዓመጽ ጠፍተዋል።


跟着我们:

广告


广告