Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 22:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ‘እነሆ፥ ከግብጽ የወጣ ሕዝብ የምድርን ፊት ሸፈነ፥ ምናልባት ልወጋው ላሳድደውም እችል እንደሆነ አሁን ና እርሱን ርገምልኝ።’ ”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ‘ከግብጽ የወጣ ሕዝብ የምድሩን ገጽ አጥለቅልቆታል፤ ስለዚህ መጥተህ ርገምልኝ፤ ምናልባት ልዋጋቸውና ላባርራቸው የምችለው ከዚያ በኋላ ሊሆን ይችላል።’ ”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ‘ከግብጽ የወጣ ሕዝብ ምድሪቱን ሸፍኖአታል፤ መጥተህ ብትረግምልኝ ምናልባት እነርሱን በጦርነት ተዋግቼ ላስወጣቸው እችል ይሆናል።’ ”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እነሆ፥ ከግ​ብፅ የወጣ ሕዝብ የም​ድ​ርን ፊት ሸፈነ፤ በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያ​ዬም ተቀ​ም​ጦ​አል፤ ምና​ል​ባት እወ​ጋው፥ አሳ​ድ​ደ​ውም ዘንድ እችል እንደ ሆነ አሁ​ንም ና እር​ሱን ርገ​ም​ልኝ።”

参见章节 复制




ዘኍል 22:11
8 交叉引用  

አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ፥ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፥ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”


በለዓምም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፦ “የሞዓብ ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ እንዲህ ብሎ ወደ እኔ ላከ፦


እግዚአብሔርም በለዓምን፦ “ከእነርሱ ጋር አትሂድ፤ የተባረከ ነውና ሕዝቡን አትረግምም” አለው።


ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “ያደረግህብኝ ምንድነው? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ ፈጽመህ ባረክሃቸው።”


በለዓምም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ባላቅ ከአራም አመጣኝ፥ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ‘ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን አውግዝልኝ አለኝ።’


የባላቅም ቁጣ በበለዓም ላይ ነደደ፤ እጆቹንም አጨበጨበ፤ ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፥ እነሆም፥ ሦስት ጊዜ ፈጽመህ ይኸው ባረክሃቸው፤


እኔ ግን በለዓምን መስማት አልፈለግሁም፤ እርሱም ፈጽሞ ባረካችሁ፥ እኔም ከእጁ አዳንኋችሁ።


ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፥ “በትር ይዘህ የምትመጣብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው፤ በአማልክቱም ስም ረገመው።


跟着我们:

广告


广告