ዘኍል 11:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 ሥጋውም ገና በጥርሳቸው መካከል ሳለ ሳይታኘክ የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ ጌታም ሕዝቡን እጅግ ታላቅ በሆነ መቅሠፍት መታ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም33 ነገር ግን ሥጋው ገና በጥርስና በጥርሳቸው መካከል ሳለ አላምጠው ሳይውጡት የእግዚአብሔር ቍጣ በላያቸው ነደደ፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ መቅሠፍት ክፉኛ መታ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 የሚበሉት ሥጋ ገና በብዛት ሳለ፥ እግዚአብሔር በሕዝቡ እጅግ ተቈጣ፤ ብርቱ መቅሠፍትም በሕዝቡ መካከል አመጣ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 ሥጋውም ገና በጥርሳቸው መካከል ሳለ ሳያኝኩትም፥ እግዚአብሔር ሕዝቡን እጅግ ታላቅ በሆነ መቅሠፍት አጠፋቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 ሥጋውም ገና በጥርሳቸው መካከል ሳለ ሳያኝኩትም፥ የእግዚአብሔር ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ መቅሠፍት እጅግ መታ። 参见章节 |