Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 10:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ ሁሉ እንዲህ ይል ነበር፦ “አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ታቦቱ ለጕዞ በተነሣ ጊዜ ሁሉ ሙሴ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ! ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ” ይል ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 የቃል ኪዳኑ ታቦት በተንቀሳቀሰ ጊዜ ሁሉ ሙሴ “እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ሁሉ ከፊትህ ይባረሩ!” ይል ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ባረ​ፈም ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ወደ እስ​ራ​ኤል እልፍ አእ​ላ​ፋት ተመ​ለስ” ይል ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ ይል ነበር።

参见章节 复制




ዘኍል 10:35
10 交叉引用  

አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።


ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፥ አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥ የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።


ድሀ ለዘለዓለም አይረሳምና፥ የችግረኞችም ተስፋቸው ለዘለዓለም አይጠፋም።


በክፉዎች ላይ ለእኔ የሚነሣ ማን ነው? ዓመፅንስ በሚያደርጉ ላይ ለእኔ የሚከራከር ማን ነው?


የጌታ ክንድ ሆይ! ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?


የሚያንጸባርቅ ሰይፌን ከሳልኩ፥ እጄም ለፍርድ ካነሳችው፥ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፥ ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እመልሳለሁ።


የሚጠሉትን በማጥፋት በፊታቸው ብድራት ይመልስባቸዋል፥ ለሚጠላው አይዘገይም፥ በፊቱ ብድራት ይመልስበታል።


ሠራዊቱ ወደ ሰፈር በተመለሰ ጊዜ የእስራኤል አለቆች፥ “ዛሬ ጌታ በፍልስጥኤማውያን እንድንሸነፍ ያደረገን ለምንድን ነው? አብሮን እንዲወጣ፥ ከጠላቶቻችንም እጅ እንዲያድነን የጌታን የኪዳኑን ታቦት ከሴሎ እናምጣ” አሉ።


跟着我们:

广告


广告