Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 1:54 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

54 የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረጉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

54 እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ይህን ሁሉ አደረጉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

54 ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉን ነገር አደረጉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

54 የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙ​ሴና ለአ​ሮን ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

54 የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረጉ።

参见章节 复制




ዘኍል 1:54
17 交叉引用  

የእስራኤልም ልጆች ሄዱ፥ እንዲሁም አደረጉ፤ ጌታ ሙሴንና አሮንን እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉ።


የመገናኛው ድንኳን የማደሪያው ሥራ ሁሉ ተጠናቀቀ። የእስራኤልም ልጆች ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ልክ እንደዛው አድርገው ሠሩ፤ እንዲሁ አደረጉ።


ሙሴም ሥራውን ሁሉ አየ፥ እነሆ ልክ ጌታ እንዳዘዘው አድርገውት ነበር፤ እንዲሁ አድርገውት ነበር፤ ሙሴም ባረካቸው።


ሙሴም ጌታ እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ፥ እንዲሁም አደረገ።


ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ፥ ወደ መሠዊያውም በሚቀርቡበት ጊዜ ይታጠቡ ነበር።


ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ በሲና ምድረ በዳ ቈጠራቸው።


ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ጉባኤ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ ሌዋውያን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይስፈሩ፤ ሌዋውያንም የምስክሩን ማደሪያ ይጠብቁ።”


ጌታም ለሙሴና ለአሮን እንዲህ ብሎ ተናገረ፦


የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ በዓላሞቻቸው አጠገብ ሰፈሩ፥ እንዲሁም በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች እየሆኑ ተጓዙ።


ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች አደረጉ።


ሙሴና አሮን የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲሁ በሌዋውያን ላይ አደረጉ፤ ጌታ ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉላቸው።


ደመናውም ሁለት ቀን ወይም አንድ ወር ወይም ረጅም ጊዜ ቆይቶ በማደሪያው ላይ ቢቀመጥ የእስራኤል ልጆች በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር፤ ነገር ግን በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።


በመጀመሪያውም ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በሲና ምድረ በዳ የፋሲካን በዓል አከበሩ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ።


ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው፤ እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


“እኔ ያዘዝሁህን ሁሉ ጠብቅ፤ በእርሱ ላይ ምንም አትጨምር፤ ከእርሱም አንዳች ነገር አትቀንስ።”


ሳሙኤልም፦ “ጌታ ለቃሉ በመታዘዝ ደስ የሚለውን ያህል፥ ጌታ፥ በሚቃጠል ቁርባንና መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ! መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም ከአውራ በግ ሥብ ይበልጣል።


跟着我们:

广告


广告