Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 5:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እንዲህ የሚሉ ነበሩ፦ “እኛ፥ ወንዶች ልጆቻችንና ሴቶች ልጆቻችን ብዙ ነን፤ እንድንበላና በሕይወት እንድንኖር እህልን እንውሰድ”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አንዳንዶቹ፣ “እኛም ሆነ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን በቍጥር ብዙ ነን፤ ታዲያ ለመብላትም ሆነ በሕይወት ለመቈየት እህል ማግኘት አለብን” አሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከእነርሱም አንዳንዶቹ “ብዙ ቤተሰብ ስላለን ሕይወታችንን ለማትረፍ የሚያስችለን እህል እንፈልጋለን” አሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “ከወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ጋር ብዙ​ዎች ነን፤ በል​ተ​ንም በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ን​ኖር እህ​ልን እን​ሸ​ምት” የሚሉ ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አያሌዎቹም፦ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ብዙዎች ናቸው፥ በልተንም በሕይወት እንድንኖር እህልን እንሸምት ይሉ ነበር።

参见章节 复制




ነህምያ 5:2
11 交叉引用  

ራቡ በመላው ዓለም ጸንቶ ስለ ነበር፥ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ ከዮሴፍ ዘንድ እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ምድር መጡ።


በግብጽ እህል መኖሩን ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ከመሞት መሰንበት ይሻላልና ወደዚያው ወርዳችሁ እህል ሸምቱልን” አላቸው።


ይሁዳም አባቱን እስራኤልን እንዲህ አለው “ልጁን ከእኔ ጋር ስደደው፤ እኛም በቶሎ እንሂድ፤ ይህ ከሆነ፥ አንተም፥ እኛም፥ ልጆቻችንም አንሞትም፤ እንተርፋለን።


እኛ በፈትህ ስለምን እንሞታለን? ምድራችንስ ስለምን ትጠፋለች? እኛንም ምድራችንንም በእህል ግዛን፥ እኛም ለፈርዖን ባርያዎች እንሁን፥ ምድራችንም ለእርሱ ትሁን፥ እኛ እንድንድን እንዳንሞትም ምድራችንም እንዳትጠፋ ዘር ስጠን።”


የነቢያት ጉባኤ አባል የነበረ ባሏ የሞተባት አንዲት ሴት ወደ ኤልሳዕ መጥታ “ጌታዬ ሆይ! ባሌ ሞቶብኛል! እርሱም አንተ እንደምታውቀው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ለባሌ ገንዘብ አበድሮት የነበረ አንድ ሰው በባሌ ዕዳ ፈንታ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ወስዶ ባርያ አድርጎ ሊገዛቸው ፈልጎአል” አለችው።


እንዲህ የሚሉም ነበሩ፦ “በራቡ ጊዜ እህል እንድንወስድ እርሻችን፥ የወይን ቦታችንንና ቤታችንን አስይዘናል”


ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፤ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልሰከራችሁም፤ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ለማስቀመጥ ደመወዙን ተቀበለ።


“ባትሰሙ፥ ለስሜም ክብር ለመስጠት በልባችሁ ባታኖሩት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “እርግማን እልክባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማለሁ፤ አሁንም ረግሜዋለሁ ምክንያቱም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና።”


“ለወንድምህ በወለድ አታበድር፥ የብር ወይም የእህል ወይም የማናቸውንም ነገር ሁሉ ወለድ አትውሰድ።


跟着我们:

广告


广告