Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 4:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እንዲሁም ደግሞ በዚያ ጊዜ ሕዝቡን፦ “በሌሊት ጠባቂዎች፥ በቀንም ሥራ እንዲሰሩልን እያንዳንዱ ከአገልጋዩ ጋር በኢየሩሳሌም ውስጥ ይደር፤” አልኋቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከዚያ ቀን ጀምሮ ከሰዎቼ እኩሌቶቹ ሥራውን ሠሩ፤ የቀሩት ደግሞ ጋሻና ጦር፣ ቀስትና ጥሩር ይዘው ነበር። የጦር አለቆች ከመላው የይሁዳ ሕዝብ በስተኋላ ቆሙ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህም ጊዜ ጀምሮ እኔ ያሰለፍኳቸው ሰዎች እኩሌቶቹ ሲሠሩ፥ እኩሌቶቹ ጥሩር ለብሰው፥ ጦር ይዘው፥ ጋሻ አንግበው፥ ቀስት ደግነው ዘብ በመቆም እንዲጠብቁ አደረግሁ፤ መሪዎቻችንም ለሕዝቡ ሙሉ ድጋፍ ይሰጡ ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ እኩ​ሌ​ቶቹ ብላ​ቴ​ኖች ሥራ ይሠሩ ነበር፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም ጋሻና ጦር፥ ቀስ​ትና ጥሩ​ርም ይዘው በፊ​ትና በኋላ ይጠ​ብቁ ነበር፤ አለ​ቆ​ቹም ከይ​ሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከዚያም ቀን ጀምሮ እኩሌቶቹ ብላቴኖቼ ሥራ ይሠሩ ነበር፥ እኩሌቶቹም ጋሻና ጦር ቀስትና ጥሩርም ይዘው ነበር፥ አለቆቹም ከይሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር።

参见章节 复制




ነህምያ 4:16
8 交叉引用  

እኛ ሥራውን ሠራን፤ እኩሌቶቹ ደግሞ ጎሕ ሲቀድ ጀምሮ ከዋክብት እስኪወጡ ድረስ ጦር ይይዙ ነበር።


እኔ፥ ወንድሞቼ፥ ጎበዛዝቶቼና ከኋላዬ የነበሩት ጠባቂዎች ልብሳችንን አናወልቅም ነበር። ወደ ውኃም ስንሄድ እያንዳንዱ መሣሪያውን ይዞ ይሄድ ነበር።


ከእኔ ጋር ይኖሩ ዘንድ ዐይኖቼ በምድር ምእመናን ላይ ናቸው፥ በቀና መንገድ የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል።


መሃሉ ላይ ራስ ማስገቢያ አንገትጌ ይኑረው፤ እንዳይቀደድም የአንገትጌው ዙሪያ የተጠለፈ ይሁን።


ሁሉም ሰይፍ የያዙና ጦርነት የለመዱ ናቸው፥ በሌሊት ከሚከሰት አደጋ የተነሣ ሰው ሁሉ ሰይፉ በወገቡ አለ።


ፈረሰኞች ሆይ! ፈረሶችን ለጉሙና ውጡ፥ ራስ ቁርንም ደፍታችሁ በቦታችሁ ቁሙ፤ ጦርንም ሰንግሉ ጥሩርንም ልበሱ።


跟着我们:

广告


广告