Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 13:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እኔም አስመሰከርሁባቸውና፦ በቅጥሩ ውጭ ለምን ታድራላችሁ? እንደገና ብታደርጉት እጆቼን አነሣባችኋለሁ አልኋቸው። ከዚያም ወዲያ በሰንበት ቀን እንደገና አልመጡም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እኔ ግን፣ “ከቅጥሩ ውጭ የምታድሩት ለምንድን ነው? እንዲህ ያለውን ነገር ዳግመኛ ብታደርጉ እጄን አነሣባችኋለሁ” ስል አስጠነቀቅኋቸው፤ እነርሱም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በሰንበት ቀን አልመጡም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እኔም “ማለድ ብላችሁ ለመግባት በማሰብ በዚያ ማደራችሁ ጥቅም የለውም፤ እንዲህ ማድረጋችሁን የምትቀጥሉ ከሆነ በእናንተ ላይ የኀይል እርምጃ ለመውሰድ እገደዳለሁ” ብዬ አስጠነቀቅኋቸው፤ ከዚያን ጊዜም ጀምሮ በሰንበት ቀን መምጣታቸውን አቆሙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እኔም አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ሁ​ባ​ቸ​ውና፥ “ከቅ​ጥሩ ውጭ ለምን ታድ​ራ​ላ​ችሁ? እንደ ገና ብታ​ደ​ር​ጉት እጆ​ችን አነ​ሣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ” አል​ኋ​ቸው። ከዚ​ያም ጊዜ ጀምሮ በሰ​ን​በት ቀን እንደ ገና አል​መ​ጡም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እኔም አስመሰከርሁባቸውና፦ በቅጥሩ ውጭ ለምን ታድራላችሁ? እንደ ገና ብታደርጉት እጆቼን አነሣባችኋለሁ አልኋቸው። ከዚያም ወዲያ በሰንበት ቀን እንደ ገና አልመጡም።

参见章节 复制




ነህምያ 13:21
6 交叉引用  

የአምላክህን ሕግና የንጉሡን ትእዛዝ በማያደርግ በማንም ላይ ሞት ወይም ስደት ወይም ንብረት መወረስ ወይም ግዞት በፅኑ ይፈረድበት።”


የምድሪቱ ሕዝቦች ሸቀጥ ወይም ልዩ ልዩ እህል ለመሸጥ በሰንበት ቀን ቢያመጡ፥ በሰንበት ወይም በተቀደሰ ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ በሰባተኛው ዓመትም ምድሪቱን እናሳርፋታለን፥ ዕዳንም ሁሉ እንሰርዛለን።


በዚያም ወራት በይሁዳ በሰንበት ቀን የወይን መጥመቂያን የሚረግጡትን፥ ነዶም የሚከመሩትን፥ የወይኑን ጠጅና የወይኑን ዘለላ በለሱንም ልዩ ልዩም ዓይነት ሸክም በአህዮች ላይ የሚጭኑትን፥ በሰንበትም ቀን ወደ ኢየሩሳሌም የሚያስገቡትን አየሁ፥ ገበያ ባደረጉበትም ቀን አስመሰከርሁባቸው።


ሁሉም አንድ ወይም ሁለት ጊዜ በኢየሩሳሌም ውጭ አድረው ገበያ አድርገው ነበር።


ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ለአገረ ገዢዎችም ቢሆን ታዘዙ።


跟着我们:

广告


广告