Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 13:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ከዚህ በኋላ ከሰንበት በፊት በኢየሩሳሌም በሮች ድንግዝግዝታ በሆነ ጊዜ በሮችዋ እንዲዘጉ፥ ሰንበትም እስኪያልፍ ድረስ እንዳይከፈቱ አዘዝሁ። በሰንበትም ቀን ሸክም እንዳይገባ ከብላቴኖቼ በአያሌዎቹ በሮችዋን አስጠበቅሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በሰንበት ዋዜማ በኢየሩሳሌም በሮች ላይ የምሽቱ ጥላ ማረፍ ሲጀምር በሮቹ እንዲዘጉና፣ ሰንበት እስኪያልፍ ድረስ እንዳይከፈቱ አዘዝሁ፤ በሰንበት ቀን ጭነት እንዳይገባም ከራሴ ሰዎች አንዳንዶቹን በየበሩ ላይ አቆምሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከዚህም በኋላ በሰንበት ዋዜማ መሸትሸት ሲል የከተማይቱ ቅጽር በሮች እንዲዘጉና የሰንበት ቀን ከማለፉም በፊት እንዳይከፈቱ ትእዛዝ ሰጠሁ፤ በሰንበት ቀን ወደ ከተማይቱ ምንም ሸክም እንዳይገባ ይቈጣጠሩ ዘንድ ከአገልጋዮቼ አንዳንዶቹን በቅጽር በሮች አሰማራሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ከዚህ በኋላ ሰን​በት ከመ​ግ​ባቱ በፊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሮች ድን​ግ​ዝ​ግ​ዝታ በሆነ ጊዜ በሮ​ችዋ እን​ዲ​ዘጉ፥ ሰን​በ​ትም እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ እን​ዳ​ይ​ከ​ፈቱ አዘ​ዝሁ። በሰ​ን​በ​ትም ቀን ሸክም እን​ዳ​ይ​ገባ ከብ​ላ​ቴ​ኖች በዐ​ያ​ሌ​ዎቹ በሮ​ች​ዋን አስ​ጠ​በ​ቅሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ከዚህ በኋላ ከሰንበት በፊት በኢየሩሳሌም በሮች ድንግዝግዝታ በሆነ ጊዜ በሮችዋ እንዲዘጉ፥ ሰንበትም እስኪያልፍ ድረስ እንዳይከፈቱ አዘዝሁ። በሰንበትም ቀን ሸክም እንዳይገባ ከብላቴኖቼ በአያሌዎቹ በሮችዋን አስጠበቅሁ።

参见章节 复制




ነህምያ 13:19
7 交叉引用  

ሁሉም አንድ ወይም ሁለት ጊዜ በኢየሩሳሌም ውጭ አድረው ገበያ አድርገው ነበር።


እኔም እንዲህ አልኋቸው፦ የኢየሩሳሌም በሮች ፀሐይ ሞቅ እስኪል ድረስ አይከፈቱ፥ በሚቆሙበት ጊዜ በሮቹን ይዝጉ፥ ይቆልፉትም፤ ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዱን በተራው አንዳንዱን ደግሞ በየቤቱ አጠገብ ጠባቂዎች ይሾሙ።


“የምድራችሁንም መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ እስከ እርሻችሁ ድንበር ድረስ ፈጽማችሁ አትሰብስቡ። የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ፤ ለድሀውና ለእንግዳው ተዉት። እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።”


ለእናንተ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ ራሳችሁንም አዋርዱ፤ በወሩ በዘጠነኛው ቀን ከማታ ጀምሮ፥ ከማታ እስከ ማታ ድረስ ሰንበታችሁን አድርጉ።”


ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው “ሰንበት ነው፥ አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም፤” አሉት።


跟着我们:

广告


广告