Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 13:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከይሁዳም ታላላቆች ጋር ተከራከርሁና፦ ይህ የምታደርጉት ክፉ ነገር ምንድነው? የሰንበትንስ ቀን ታረክሳላችሁን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እኔም የይሁዳን መኳንንት በመገሠጽ እንዲህ አልኋቸው፤ “ሰንበትን በማርከስ ይህ የምትፈጽሙት ክፉ ድርጊት ምንድን ነው?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እኔም የአይሁድ መሪዎችን በመገሠጽ እንዲህ አልኳቸው፥ “የምታደርጉትን ክፉ ነገር ሁሉ ተመልከቱ! እነሆ ሰንበትን እያረከሳችኋት ነው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከይ​ሁ​ዳም አለ​ቆ​ችና ታላ​ላ​ቆች ጋር ተከ​ራ​ከ​ር​ሁና እን​ዲህ አል​ኋ​ቸው፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ክፉ ነገር ምን​ድን ነው? የሰ​ን​በ​ት​ንስ ቀን ታረ​ክ​ሳ​ላ​ች​ሁን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከይሁዳም ታላላቆች ጋር ተከራከርሁና፦ ይህ የምታደርጉት ክፉ ነገር ምንድር ነው? የሰንበትንስ ቀን ታረክሳላችሁን?

参见章节 复制




ነህምያ 13:17
14 交叉引用  

እኔም፦ የእግዚአብሔር ቤት ስለምን ተተወ? ብዬ ከአለቆቹ ጋር ተከራከርሁ። ሰበሰብኋቸውም፥ በየስፍራቸውም አቆምኋቸው።


ደግሞም በእርሷ የተቀመጡ የጢሮስ ሰዎች ነበሩ፥ እነርሱም ዓሣዎችን ልዩ ልዩም ዓይነት ሸቀጥ አምጥተው በሰንበት ቀን በኢየሩሳሌም ለይሁዳ ልጆች ይሸጡ ነበር።


ከእነርሱም ጋር ተከራከርሁ፥ ረገምኋቸውም፥ ከእነርሱም አያሌዎቹን መታሁ፥ ጠጉራቸውንም ነጨሁ፥ እንዲህም ብዬ በእግዚአብሔር አማልኋቸው፦ ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለእናንተና ለልጆቻችሁ አትውሰዱ።


በልቤም አሰብሁና መኳንንቶቹንና ሹማምቱን ተከራከርኋቸው፥ እንዲህም አልኋቸው፦ “እያንዳንዳችሁ ለወንድማችሁ በአራጣ ታበድራላችሁ”፤ ትልቅ ጉባኤም ሰበሰብሁባቸው።


ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያመሰግናሉ፥ ሕግ ጠባቂዎች ግን ይቃወሟቸዋል።


እናንተ የሰዶም ገዦች፤ የጌታን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሰዎች፤ የእግዚአብሔርን ሕግ አድምጡ።


ለንጉሡና ለንጉሥ እናት ለእቴጌይቱ፦ “የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ተዋርዳችሁ ተቀመጡ” በል።


ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ እነርሱንም አናግራቸዋለሁ፤ የጌታን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና” አልሁ። እነዚህ ግን ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፥ እስራቱንም ቈርጠዋል።


ነገር ግን የእስራኤል ቤት በምድረ በዳ ዐመፁብኝ፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ፍርዴን ጣሱ፥ በትእዛዜም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ፦ አጠፋቸው ዘንድ ቁጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።


“ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በባልንጀራህ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ በጽኑ ገሥጸው።


እንዲህም አልሁ፦ የያዕቆብ አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዢዎች ሆይ፥ እባካችሁ ስሙኝ! ፍትሕን ማወቅ አይገባችሁምን?


ፍትሕን የምትጠሉ፥ ትክክለኛውንም ነገር ሁሉ የምታጣምሙ እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዢዎች ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ስሙ፦


跟着我们:

广告


广告