ነህምያ 12:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ ላይ አወጣኋቸው፥ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፥ አንዱም ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣያው በር ሄደ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም31 እኔም የይሁዳን መሪዎች በቅጥሩ ግንብ ዐናት ላይ እንዲወጡ አደረግሁ፤ ደግሞም ምስጋና እንዲያቀርቡ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን መደብሁ። አንዱ በቅጥሩ ግንብ ዐናት በስተቀኝ በኩል ቈሻሻ መጣያ በር ወደሚባለው ሄደ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 እኔም ነህምያ የይሁዳን መሪዎች በቅጽሩ ላይ እንዲወጡ ካደረግሁ በኋላ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን የምስጋና መዝሙር እንዲዘምሩ አደረግሁ፤ የመጀመሪያው ቡድን በቅጽሩ ግንብ አናት ላይ በስተቀኝ በኩል ወደሚገኘው ወደ ጒድፍ መጣያው የቅጽር በር በኩል አለፈ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ አወጣኋቸው፤ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፤ የአንዱም ተርታ ሰዎች ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣያው በር ሄዱ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ ላይ አወጣኋቸው፥ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፥ አንዱም ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጕድፍ መጣያው በር ሄደ። 参见章节 |