Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 12:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሻብያ፥ ሼሬብያ፥ የቃድሚኤል ልጅ ኢያሱና ወንድሞቻቸው ደግሞ ከፊት ለፊታቸው ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ክፍል በክፍል ትይዩ ሆነው ያወድሱና ያመሰግኑ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድምኤል ልጅ ኢያሱ ነበሩ፤ እነርሱም ከወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት እየተቀባበሉ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ሌዋውያኑ በሐሻብያ፥ በሼሬብያ፥ በኢያሱ፥ በቢኑይና በቃድሚኤል መሪነት በሁለት ቡድኖች ተከፈሉ። ሁለቱም ቡድኖች የእግዚአብሔር ሰው የሆነ ንጉሥ ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እየተቀባበሉ የምስጋና መዝሙር በማቅረብ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አለ​ቆች አሳ​ብያ፥ ሰር​ብያ፥ ኢያሱ፥ የቀ​ድ​ም​ኤ​ልም ልጆች፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእ​ዛዝ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው በእ​ነ​ርሱ ፊት ያከ​ብ​ሩና ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የሌዋውያኑም አለቆች ሐሸብያ፥ ሰራብያ፥ የቀድምኤልም ልጅ ኢያሱ እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።

参见章节 复制




ነህምያ 12:24
18 交叉引用  

ሴትዮዋም “እነሆ አንተ የእግዚአብሔር ሰው መሆንህንና በአፍህ ያለው የጌታ ቃል እውነት እንደሆነ አሁን አወቅሁ!” ስትል መለሰችለት።


በጌታም ታቦት ፊት እንዲያገለግሉ፥ የእስራኤልንም አምላክ ጌታን እንዲወድሱት፥ እንዲያመሰግኑትና እንዲያከብሩትም ከሌዋውያን ወገን ሾመ።


የጌታም ሰው ዳዊት እንዲህ አዝዞ ነበርና ካህናቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥርዓት በየአገልግሎታቸው ሰሞን ከፈላቸው፤ ሌዋውያንም እንደ ሥርዓታቸው እንዲያመሰግኑ፥ በካህናቱም ፊት እንዲያገለግሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው፤ ጠባቂዎችንም ደግሞ በየበሩ ሁሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው።


ሌዋውያኑ፥ ከሆዳቭያ ወገን የኢያሱና የቃድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት።


ምስጋናውን በጸሎት ለመጀመር መሪ የነበረው የአሳፍ ልጅ፥ የዛብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታንያ፤ ከወንድሞቹ ሁለተኛ የነበረው ባቅቡቅያ፤ የይዱቱን ልጅ፥ የጋላል ልጅ፥ የሻሙዓ ልጅ ዓብዳ።


የሌዊ ልጆች የአባቶች መሪዎች እስከ ኤልያሺብ ልጅ እስከ ዮሐናን ዘመን ድረስ በታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ነበር።


ወንድሞቹም ሸማዕያ፥ ዓዛርኤል፥ ሚላላይ፥ ጊላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳና ሐናኒ የእግዚአብሔር ሰው የዳዊትን የዜማ መሣሪያ ይዘው ሄዱ፤ ጸሐፊው ዕዝራም በፊታቸው ነበረ።


ደግሞ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ሼሬብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሻብታይ፥ ሆዲያ፥ ማዓሤያ፥ ቅሊጣ፥ አዛርያ፥ ዮዛባድ፥ ሐናን፥ ፐላያና ሌዋውያኑ ሕጉን ለሕዝቡ ያስረዱ ነበር፤ ሕዝቡም በቆሙበት ነበሩ።


በሌዋውያኑ መድረክ ላይ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ቃድምኤል፥ ሽባንያ፥ ቡኒ፥ ሼሬብያ፥ ባኒ፥ ክናኒ ቆመው ወደ ጌታ አምላካቸው በታላቅ ድምፅ ጮኹ።


የጌታ ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት የእስራኤልን ሕዝብ የባረከበት ቃለ ቡራኬ ይህ ነው።


የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! አንተ ግን ከእነዚህ ነገሮች ሽሽ፤ ጽድቅን፥ እግዚአብሔርን መምሰልን፥ እምነትን፥ ፍቅርን፥ መጽናትን፥ የዋህነትን ግን ተከተል።


በዚህም የእግዚአብሔር ሰው በችሎታው ፍጹም እንዲሆንና ለመልካም ሥራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ይጠቅማል።


የይሁዳም ልጆች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ “ለእግዚአብሔር ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ ጌታ በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ።


跟着我们:

广告


广告