Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 10:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ሌዋውያኑም አሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፥ ሌዋውያኑም የአሥራቱን አሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ዐሥራቱን በሚቀበሉበት ጊዜም ከአሮን ዘር የተወለደው ካህን ከሌዋውያኑ ጋራ ዐብሮ ይገኛል፤ ሌዋውያኑም የዐሥራቱን አንድ ዐሥረኛ ወደ አምላካችን ቤት፣ ወደ ዕቃ ማከማቻ ክፍሎች ያመጡታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ዐሥራቱም በሚሰበሰብበት ጊዜ ትውልዳቸው ከአሮን ወገን የሆኑ ካህናት፥ ከሌዋውያኑ ጋር ይገኛሉ፤ ለቤተ መቅደሱም አገልግሎት ሌዋውያኑ ከሚሰበስቡት ዐሥራት ውስጥ እንደገና ከዐሥር አንዱን አወጣጥተው ወደ ቤተ መቅደሱ የዕቃ ግምጃ ቤት ያስገባሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ሌዋ​ው​ያ​ኑም ዐሥ​ራ​ቱን በተ​ቀ​በሉ ጊዜ የአ​ሮን ልጅ ካህኑ ከሌ​ዋ​ው​ያን ጋር ይሁን፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም የዐ​ሥ​ራ​ቱን ዐሥ​ራት ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ወደ ጓዳ​ዎች ወደ ዕቃ ቤት ያም​ጡት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ሌዋውያኑም አሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፥ ሌዋውያኑም የአሥራቱን አሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት።

参见章节 复制




ነህምያ 10:38
11 交叉引用  

ከሌዋውያንም የነበሩ አራቱ የጠባቂዎች አለቆች በሥራቸው ታማኞች ነበሩ፤ በጌታም ቤት ባሉ ጓዳዎችና ቤተ መዛግብት ላይ ተሹመው ነበር።


በየጊዜውም ለእንጨት ቁርባን ለበኩራቱም ሥርዓት አደረግሁ። አምላኬ ሆይ፥ በመልካም አስበኝ።


“የምድሪቱም አሥራት ሁሉ፥ ከምድሪቱ ዘር ወይም ከዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የጌታ ነው፤ ለጌታ የተቀደሰ ነው።


እናንተ የምድሪቱን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ለጌታ እንደ ልዩ ስጦታ የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ።


መጀመሪያ ከምታዘጋጁት ሊጥ እንደ ስጦታ አድርጋችሁ የምታቀርቡትን ቁርባን እስከ ልጅ ልጃችሁ ለጌታ ትሰጣላችሁ።


ለሌዊም ልጆች፥ እነሆ፥ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች አሥራት ሁሉ ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ።


ለጌታ እንደ ስጦታ ቁርባን የሚያቀርቡትን የእስራኤልን ልጆች አሥራት ለሌዋውያን ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ፤ ስለዚህ፦ በእስራኤል ልጆች መካከል ርስት አይወርሱም አልኋቸው።”


“በየዓመቱ ከእርሻህ ከምታገኘው ምርት ከዐሥር አንዱን እጅ ለይተህ አስቀምጥ።


跟着我们:

广告


广告