ነህምያ 10:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)36 በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት፥ በአምላካችን ቤት ወደ ሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም36 “እንዲሁም በሕጉ እንደ ተጻፈው የወንድ ልጆቻችንንና፣ የቀንድ ከብቶቻችንን፣ የመንጋዎቻችንን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻችንን በኵራት ወደ አምላካችን ቤት፣ ወደሚያገለግሉትም ካህናት እናመጣለን። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም36 ከእኛ እያንዳንዳችን የሚወለደውን የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን በማስረከብ፥ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን እናደርጋለን፤ እንዲሁም ከላሞቻችን፥ ከበጎቻችንና ከፍየሎቻችን የሚወለደውንም ጥጃና ግልገል ሁሉ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር እንለያለን። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)36 በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)36-37 በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንና የእንስሶቻችንን በኩራት፥ የበሬዎችቻችንንና የበጎቻችንን በኩራት፥ በአምላካችን ቤት ወደ ሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥ የእህላችንንም በኩራት፥ የእጅ ማንሣታችንን ቁርባን፥ የዛፍ ሁሉ ፍሬ፥ ወይኑንና ዘይቱንም ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ አሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን አሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን። 参见章节 |