ነህምያ 1:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 እንዲህም አልሁ፦ ታላቅና የተፈራ አምላክ፥ ለሚወድዱትና ትእዛዙን ለሚጠብቁ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የሚጠብቅ፥ የሰማይ አምላክ ጌታ ሆይ፥ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ከዚያም እንዲህ አልሁ፤ “ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያከብሩ የፍቅርህን ቃል ኪዳን የምትጠብቅ ታላቅና የተፈራህ አምላክ፣ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 “እግዚአብሔር የሰማይ አምላክ ሆይ! አንተ ታላቅ ነህ፤ እኛም በፍርሃት በፊትህ እንቆማለን፤ አንተ ከሚወዱህና ትእዛዞችህንም ከሚጠብቁ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳንህን ትጠብቃለህ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 “አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ፥ ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ፥ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 እንዲህም አልሁ፦ “አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ፥ ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ፥ 参见章节 |