Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ናሆም 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ፈረሰኛው ይጋልባል፥ ሰይፍ ይንቦገቦጋል፥ ጦር ይብለጨለጫል የተገደለ ብዛት፥ የበድን ክምር፥ ሬሳው ማለቂያ የለውም፤ በሬሳቸውም ይሰናከላሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ፈረሰኛው ይጋልባል፤ ሰይፍ ይንቦገቦጋል፤ ጦር ያብረቀርቃል። የሞተው ብዙ ነው፤ ሬሳ በሬሳ ሆኗል፤ ስፍር ቍጥር የለውም፤ መተላለፊያ አልተገኘም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ፈረሰኞች ወደፊት እየገፉ የሚያብረቀርቅ ሰይፋቸውንና የሚያብለጨልጭ ጦራቸውን ያነሣሉ፤ ብዙ ሰዎች ስለ ተገደሉ ሬሳዎች ተከምረዋል፤ ከሬሳውም ብዛት የተነሣ በዚያ የሚያልፍ ሰው ሁሉ ይደናቀፋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ፈረሰኛው ይጋልባል፥ ሰይፍም ይንቦገቦጋል፥ ጦርም ይብለጨለጫል፣ የተገደሉትም ይበዛሉ፥ በድኖችም በክምር ይከመራሉ፥ ሬሳቸውም አይቈጠርም፣ በሬሳቸውም ይሰናከላሉ።

参见章节 复制




ናሆም 3:3
10 交叉引用  

አዳምንም ካስወጣው በኋላ፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በሁሉም አቅጣጫ የምትውለበለብ ነበልባላዊ ሰይፍን በዔድን ገነት በስተ ምሥራቅ አስቀመጠ።


በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ።


ከእነርሱም የተገደሉት ይጣላሉ። ሬሳቸውም ይከረፋል፤ ተራሮችም በደማቸው ይርሳሉ።


የጌታም መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።


ጌታም በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፉ ይፈርዳል፤ በጌታም ተወግተው የሞቱት ይበዛሉ።


አንተ፥ ወታደሮችህና ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ ሁሉ በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ፤ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።


ማንም ሳያሳድዳቸው ከሰይፍ እንደሚሸሹ እርስ በርሳቸው ይሰነካከላሉ፤ እናንተም በጠላቶቻችሁ ፊት የምትቆሙበት ኃይል አይኖራችሁም።


የጦረኞቹ ጋሻ ቀልቶአል፥ ኃያላን ሰዎችም ቀይ ልብስ ለብሰዋል። እርሱ በሚያዘጋጅበት ቀን ሰረገሎች እንደ እሳት ይንቦገቦጋሉ፥ ጦሮቹም ይወዘወዛሉ።


በቀስቶችህ ብርሃን፥ በጦርህ መብረቅ ፀዳል፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቀጥ ብለው ቆሙ።


跟着我们:

广告


广告