Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ናሆም 2:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ነነዌ በዘመኗ ሁሉ እንደ ተከማቸ ውኃ ነበረች፤ እርሱም እየደረቀ ነው። “ቁሙ፥ ቁሙ” ይላሉ፥ ነገር ግን የሚመለስ የለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ብሩን ዝረፉ! ወርቁን ንጠቁ! በየግምጃ ቤቱ ያለው፣ የተከማቸውም ሀብት ስፍር ቍጥር የለውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የከተማይቱ ሀብት መጨረሻ የለውም፤ የከበሩ ድንጋዮቹም የተትረፈረፉ ናቸው፤ ስለዚህ ሄዳችሁ ብሩንና ወርቁን በዝብዛችሁ ውሰዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 መዝገብዋ መጨረሻ የለውምና፥ የከበረውም የዕቃዋ ሁሉ ብዛት አይቈጠርምና ብሩን በዝብዙ፥ ወርቁንም በዝብዙ።

参见章节 复制




ናሆም 2:9
12 交叉引用  

ዓመቱ ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደናፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፥ የከበረውንም የጌታን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ ወንድሙንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።


አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፥ አንተም ሳትካድ ክህደትን የምትፈጽም ወዮልህ! ማጥፋትን በተውክ ጊዜ ትጠፋለህ፤ መካድን በተውክ ጊዜ ትካዳለህ።


አንበጣ እንደሚሰበሰብ ምርኮአችሁ ትሰብስባለች፤ ኩብኩባም እንደሚዘል ሰዎች ይዘልሉበታል።


“ልትታረዱና ልትበተኑ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደም የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች፥ አልቅሱ ጩኹም፤ እናንተ የመንጋ አውራዎች፥ በአመድ ውስጥ ተንከባለሉ።


ፈርተው ወደ ኋላ ሲመለሱ፥ ኃያላኖቻቸውም ሲደበደቡ ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዚህና በዚያ ድንጋጤ አለ፥ ይላል ጌታ።


አጥፊው በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፥ ኃያላኖችዋ ተያዙ፥ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ ጌታ ፍዳን የሚከፍል አምላክ ነውና፥ ፍዳንም በእርግጥ ይከፍላል።


ሀብትሽን ይዘርፋሉ፥ ሸቀጣ ሸቀጥሽንም ይበዘብዛሉ፤ ቅጥርሽን ያፈርሳሉ፥ የተዋቡ ቤቶችሽን ያጠፋሉ፤ ድንጋይሽን፥ እንጨትሽንና አፈርሽን በውኆች መካከል ያስቀምጣሉ።


ጠባቂዎችሽ እንደ አንበጣ፥ መኳንንቶችሽም በብርድ ቀን በቅጥር ላይ እንደ ሰፈረ የኩብኩባ መንጋ ናቸው፤ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ይበራሉ፥ ስፍራቸው የት እንደሆነ አይታወቅም።


ጭነቱም ወርቅና ብር፥ የከበረም ድንጋይ ዕንቁም፥ ቀጭንም ተልባ እግር፥ ቀይም ሐር፥ ሐምራዊም ልብስ፥ መልካም መዐዛ ያለውም እንጨት ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የተሠራ ዕቃ ሁሉ፥ እጅግም ከከበረ እንጨት፥ ከነሐስም ከብረትም ከዕብነ በረድም የተሠራ ዕቃ ሁሉ፥


“በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጐናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! ይላሉ።


跟着我们:

广告


广告