Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ናሆም 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሰረገሎች በመንገድ ላይ ይከንፋሉ፥ በአደባባዮችም ወዲህና ወዲያ ይጣደፋሉ፤ መልካቸው እንደ ፋና ነው፥ እንደ መብረቅም ይወረወራሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ምርጥ ተዋጊዎቹን ይጠራል፤ ዳሩ ግን መንገድ ላይ ይሰናከላሉ፤ ወደ ከተማዪቱ ቅጥር ይሮጣሉ፤ መከላከያ ጋሻውም በቦታው አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እርሱ የጦር ሹማምንቱን ይጠራል፤ እነርሱም እየተደናቀፉ ወደፊት ይመጣሉ፤ የጠላት ወታደሮች እየሮጡ ወደ ከተማይቱ ቅጽር ይወጣሉ፤ የሚወረወርባቸውንም ፍላጻ በትልቁ ጋሻቸው ይከላከላሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 መሳፍንቱን ያስባል፣ በአረማመዳቸው ይሰናከላሉ፣ ፈጥነው በቅጥርዋ ላይ ይወጣሉ፥ መጠጊያም ተዘጋጀለት።

参见章节 复制




ናሆም 2:5
9 交叉引用  

ማዕዱን ያዘጋጃሉ፥ ምንጣፉንም ይዘረጋሉ፥ ይበላሉም፥ ይጠጣሉም፤ እናንተ መሳፍንት ሆይ፥ ተነሡ፥ ጋሻውን አዘጋጁ።


በመካከላቸው ደካማና ስንኩል አይገኝም፤ የሚያንቀላፋና የሚተኛ አይኖርም፤ የወገባቸው መቀነት አይላላም፤ የጫማቸውም ማሰሪያ አይበጠስም።


ኃያሉ በኃያሉ ላይ ተሰናክሎ ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና አሕዛብ ውርደትሽን ሰምተዋል፥ ልቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል።


ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት አንድም ሰው አያምልጥ፤ በእስራኤል ቅዱስ በጌታ ላይ በኩራት አልታዘዝም ብላለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፥ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።


መሳፍንቱን ያስባል፤ በአረማመዳቸው ይሰናከላሉ፤ ፈጥነው ወደ ቅጥርዋ ይሮጣሉ፥ መጠለያም ተዘጋጅቷል።


የአሦር ንጉሥ ሆይ፥ እረኞችህ አንቀላፍተዋል፤ መኳንንቶችህም ዐርፈዋል፤ ሕዝብህ በተራሮች ላይ ተበትነዋል፥ የሚሰበስባቸውም የለም።


ፈረሰኛው ይጋልባል፥ ሰይፍ ይንቦገቦጋል፥ ጦር ይብለጨለጫል የተገደለ ብዛት፥ የበድን ክምር፥ ሬሳው ማለቂያ የለውም፤ በሬሳቸውም ይሰናከላሉ።


ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኩላ ይልቅ አስፈሪዎች ናቸው፤ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ፈረሰኞቻቸው ከሩቅ ይመጣሉ፥ ለመንጠቅ እንደሚቸኩል ንስር ይበርራሉ።


跟着我们:

广告


广告