ናሆም 1:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ባሕሩንም ይገሥጻል፥ ያደርቀዋልም፥ ወንዞችን ሁሉ ያደርቃል፤ ባሳንና ቀርሜሎስም ጠውልጎአል፥ የሊባኖስም አበባ ጠውልጎአል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ባሕርን ይገሥጻል፤ ያደርቀዋልም፤ ወንዞችን ሁሉ ያደርቃል። ባሳንና ቀርሜሎስ ጠውልገዋል፤ የሊባኖስም አበቦች ረግፈዋል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እግዚአብሔር ባሕሩንና ወንዞቹን ገሥጾ ያደርቃቸዋል። በባሳንና በቀርሜሎስ የሚገኙ ዕፀዋት ይደርቃሉ፤ የሊባኖስም አበቦች ይጠወልጋሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ባሕሩንም ይገሥጻታል፥ ያደርቃትማል፥ ወንዞችንም ሁሉ ያደርቃል፣ ባሳንና ቀርሜሎስም ላልተዋል፥ የሊባኖስም አበባ ጠውልጎአል። 参见章节 |